Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘካርያስ 5:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከዚያም ዐይኖቼን አንሥቼ አየሁ፥ እነሆም፥ ሁለት ሴቶች ወጡ፥ በክንፎቻቸውም ነፋስ ነበረ፤ ክንፎቻቸውም እንደ ሽመላ ክንፎች ነበሩ፤ የኢፍ መስፈሪያውንም በምድርና በሰማይ መካከል አነሡት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከዚያም ወደ ላይ ተመለከትሁ፤ እነሆም፣ ከፊቴ ሁለት ሴቶች ነበሩ፤ በክንፎቻቸውም ነፋስ ነበር፤ ክንፎቻቸውም እንደ ሽመላ ክንፎች ነበሩ፤ የኢፍ መስፈሪያውንም በምድርና በሰማይ መካከል አነሡት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ቀና ብዬ ስመለከት እነሆ ሁለት ሴቶች እየበረሩ ወደ እኔ መጡ፤ ክንፎቻቸውም እንደ ሽመላ ክንፎች ብርቱዎች ነበሩ። እነርሱም ያንን ቅርጫት ከመሬት አንሥተው ወደ ሰማይ ይዘውት በረሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ዓይኖቼንም አንሥቼ አየሁ፥ እነሆም፥ ሁለት ሴቶች ወጡ፥ ነፋስም በክንፎቻቸው ነበረ፣ ክንፎቻቸውም እንደ ሽመላ ክንፎች ነበሩ፣ የኢፍ መስፈሪያውንም በምድርና በሰማይ መካከል አነሡት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ዓይኖቼንም አንሥቼ አየሁ፥ እነሆም፥ ሁለት ሴቶች ወጡ፥ ነፋስም በክንፎቻቸው ነበረ፥ ክንፎቻቸውም እንደ ሽመላ ክንፎች ነበሩ፥ የኢፍ መስፈሪያውንም በምድርና በሰማይ መካከል አነሡት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘካርያስ 5:9
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚያም ወፎች ጎጆአቸውን ይሠራሉ፥ ሽመላዎችም ከበላያቸው ቤታቸውን ያበጃሉ።


እንዲሁም ሽመላ በሰማይ ጊዜዋን አውቃለች፤ ዋኖስና ጨረባ ዋልያም የመምጫቸውን ጊዜ ይጠብቃሉ፤ ሕዝቤ ግን የጌታን ፍርድ አላወቁም።


መለከትን ወደ አፍህ አቅርብ፤ ቃል ኪዳኔን ተላልፈዋልና፥ በሕጌም ላይ ዐምፀዋልና እንደ ንስር በጌታ ቤት ላይ እያንዣበበ ነው።


“ከወፎችም ወገን የምትጸየፉአቸው እነዚህ ናቸው፤ አይበሉም፤ የተጸየፉ ናቸው፤ ንስር፥ ገዲ፥ ዓሣ አውጭ፥


ሽመላ፥ ሳቢሳ በየወገኑ፥ ጅንጁላቴ ወፍ፥ የሌሊት ወፍ።


ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረውን መልአክ፦ “እነዚህ የኢፍ መስፈሪያውን ወዴት ይወስዱታል?” አልኩት።


በድን ባለበት በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ።


ጌታ እንደ ንስር ፈጥኖ የሚወርድንና ቋንቋው የማታውቀውን ሕዝብ እጅግ ሩቅ ከሆነ፥ ከምድርም ዳርቻ ያስነሣብሃል፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች