Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘካርያስ 5:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “ይህ በምድር ፊት ሁሉ ላይ የሚወጣው እርግማን ነው፤ የሚሰርቅና በሐሰት የሚምልም ሁሉ በእዚህ ላይ እንደተጻፈው ይጠፋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ይህ በምድር ሁሉ ላይ የሚወጣ ርግማን ነው፤ በአንደኛው በኩል እንደ ተጻፈው የሚሰርቅ ሁሉ ይጠፋል፤ በሌላው በኩል ደግሞ እንደ ተጻፈው በሐሰት የሚምል ሁሉ ይጠፋልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “የተጠቀለለው መጽሐፍ በውስጡ በምድሪቱ ሁሉ ላይ የሚመጣው ርግማን ተጽፎበታል፤ የተጠቀለለው መጽሐፍ በአንድ በኩል ‘ሌባ ሁሉ ከምድር ይወገዳል’ የሚል ሲሆን፥ በሌላ በኩል ‘በመሐላ ሐሰት የሚናገር ሁሉ ይጠፋል’ ይላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እንዲህም አለኝ፦ ይህ በምድር ፊት ሁሉ ላይ የሚወጣው እርግማን ነው፣ የሚሰርቅ ሁሉ በእርሱ ላይ በዚህ በኩል እንደ ተጻፈው ሁሉ ይጠፋል፥ በሐሰት የሚምልም ሁሉ በእርሱ ላይ በዚያ በኩል እንደ ተጻፈው ሁሉ ይጠፋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እንዲህም አለኝ፦ ይህ በምድር ፊት ሁሉ ላይ የሚወጣው እርግማን ነው፥ የሚሰርቅ ሁሉ በእርሱ ላይ በዚህ በኩል እንደ ተጻፈው ሁሉ ይጠፋል፥ በሐሰት የሚምልም ሁሉ በእርሱ ላይ በዚያ በኩል እንደ ተጻፈው ሁሉ ይጠፋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘካርያስ 5:3
42 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከሌባ ጋር የሚካፈል ነፍሱን ይጠላል፥ መርገምን ይሰማል፥ ነገር ግን ምንም አይገልጥም።


የጌታ መርገም በክፉ ሰዎች ቤት ነው፥ የጻድቃን ቤት ግን ይባረካል።


እንዳልጠግብ እንዳልክድህም፦ “ጌታስ ማን ነው?” እንዳልል፥ ድሀም እንዳልሆን እንዳልሰርቅም፥ የአምላኬንም ስም እንዳላረክስ።


ስለዚህ መርገም ምድርን ትበላለች፥ ነዋሪዎቿም ስለ ጥፋታቸው ይቀጣሉ፤ ስለዚህ የምድር ነዋሪዎች ይቃጠላሉ ጥቂት ሰዎችም ይቀራሉ።


ስለዚህ የመቅደሱን አለቆች አረከስኩ፥ ያዕቆብንም እርግማን፥ እስራኤልንም ስድብ አደረግሁ።


እናንተ በእስራኤል ስም የተጠራችሁ ከይሁዳም ውኆች የወጣችሁ፥ በጌታ ስም የምትምሉ፥ በእውነት ሳይሆን በጽድቅም ሳይሆን የእስራኤልን አምላክ የምትጠሩ፥


ምድር በአመንዝሮች ተሞልታለችና፥ ከመርገምም የተነሣ ምድር አልቅሳለች፤ የምድረ በዳውም ማሰማርዎች ደርቀዋል፤ አካሄዳቸውም ክፉ ነው፥ ብርታታቸውም ቅን አይደለም።


ይህን ቤት እንደ ሴሎ አደርገዋለሁ፥ ይህችንም ከተማ ለምድር አሕዛብ ሁሉ እርግማን አደርጋታለሁ።’ ”


እነርሱም፦ “በሕያው ጌታ እምላለሁ!” ቢሉም እንኳ የሚምሉት በሐሰት ነው።


ትሰርቃላችሁን፥ ትገድላላችሁን፥ ታመነዝራላችሁን፥ በሐሰትም ትምላላችሁን፥ ለበዓልም ታጥናላችሁን፥ የማታውቋቸውንም እንግዶች አማልክት ትከተላላችሁን፤


ተመለከትሁም፥ እነሆ እጅ ወደ እኔ ተዘርግታ ነበር፥ እነሆ የመጽሐፍ ጥቅልል ነበረባት።


መራገምና መዋሸት፥ መግደልና መስረቅ፥ ማመንዘርም ገደባቸውን አልፈዋል፤ ደም ማፍሰስ ደም ማፍሰስን አስከትሏል።


“አትስረቁ፥ አትካዱም፥ ከእናንተም ማንም ሰው ወንድሙን አያታልል።


በስሜም በሐሰት አትማሉ፥ በዚህም የአምላካችሁን ስም አታርክሱ፤ እኔ ጌታ ነኝ።


“በንጉሥ ቅጥሮቻቸውም ግፍንና ቅሚያን የሚያከማቹ ቅን ነገር እንዴት እንደሚደረግ አያውቁም፥” ይላል ጌታ።


እኔ እልከዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፥ ወደሚሰርቀውም ቤት፥ በሐሰትም በስሜ ወደሚምለው ቤት ይገባል፤ በቤታቸውም ውስጥ ይኖራል፥ እንጨቱንና ድንጋዩን፥ ይበላል።”


አንዱ በሌላው ላይ ክፉን ነገር በልቡ አያስብ፤ የሐሰትንም መሐላ አትውደዱ፤ ይህን ነገር ሁሉ እጠላለሁና፥ ይላል የጌታ ቃል።


ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት በሚምሉ፥ የሠራተኛውን ደመወዝ በሚያስቀሩ፥ መበለቲቱንና የሙት ልጅን በሚያስጨንቁ፥ ስደተኛውን በሚገፉ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


መጥቼ ምድርን በእርግማን እንዳልመታ፥ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶቻቸው ይመልሳል።


ከዚህ በኋላ በግራው ያሉትን ደግሞ እንዲህ ይላቸዋል ‘እናንተ የተረገማችሁ! ከእኔ ወዲያ ራቁ! ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ።


በምድር ሁሉ ላይ በሚቀመጡ ሁሉ እንደ ወጥመድ ይደርስባቸዋልና።


የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፤ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖረው በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም።


ይህንንም በመረዳት ሕግ የተሠራው ለጻድቃን ሳይሆን ይልቁንስ ለበደለኞችና ለማይታዘዙ፥ ለዐመጸኞችና ለኀጢአተኞች፥ ቅድስና ለሌላቸውና ለርኩሳን፥ አባትና እናትን ለሚገድሉ፥ ለነፍሰ ገዳዮች፥


ከሁሉም በላይ ወንድሞቼ ሆይ! በሰማይ ወይም በምድር ወይም በማናቸውም ነገር ቢሆን አትማሉ፤ ነገር ግን ከፍርድ በታች እንዳትወድቁ፥ ነገራችሁ “አዎ” ቢሆን አዎ ይሁን፤ “አይደለም” ቢሆን አይደለም ይሁን።


እነሆ፥ እርሻችሁን ሲያጭዱ ለዋሉ ሠራተኞች ያልከፈላችሁት ደመወዝ በእናንተ ላይ ይጮኻል፤ የአጫጆቹም ጩኸት የሠራዊት ጌታ ጆሮ ደርሶአል።


ስለ ማልንላቸው መሓላ ቁጣ እንዳይወርድብን ይህን እናድርግባቸው፥ በሕይወትም እንዲኖሩ እንተዋቸው።”


ነገር ግን የሚፈሩ፥ የማያምኑ፥ የሚረክሱ፥ ነፍሰ የሚያጠፉ፥ የሚሴሰኑ፥ አስማትን የሚያደርጉ፥ ጣዖትንም የሚያመልኩና የሚዋሹ ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ውስጥ ነው፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”


ውሻዎችና አስማተኞች፥ ሴሰኛዎችም፥ ነፍሰ ገዳዮችም፥ ጣዖት አምላኪዎችም፥ ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ ይቀራሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች