ዘካርያስ 2:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 እኔም፦ “እነዚህ የመጡት ምን ሊሠሩ ነው?” አልኩት። እርሱም፦ “አንድ ሰው ራሱን ቀና ማድረግ እስኪሳነው ድረስ እነዚህ ቀንዶች ይሁዳን የበተኑ ናቸው፤ እነዚህ ግን ሊያስፈራሯቸው፥ የይሁዳንም አገር ለመበተን ቀንዳቸውን ያነሡትን የአሕዛብን ቀንዶች ሊቆርጡ መጥተዋል” ብሎ ተናገረ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 እንዲህም አለው፣ “ሩጥና ለዚያ ጕልማሳ እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘በውስጧ ካለው የሰውና የከብት ብዛት የተነሣ፣ ኢየሩሳሌም ቅጥር እንደሌላት ከተማ ትሆናለች፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 የመጀመሪያው መልአክ ሁለተኛውን እንዲህ አለው፦ “የመለኪያ ገመድ ወደያዘው ወጣት በሩጫ ሂድና ‘በኢየሩሳሌም ብዙ ሕዝብና ብዙ እንስሶች ስለሚገኙ ትልቅ ግንብ መሥራት ያዳግታል’ ብለህ ንገረው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ሩጥ፥ ይህንም ጕልማሳ እንዲህ በለው፦ ኢየሩሳሌም በውስጥዋ ካሉት ሰዎችና እንስሶች ብዛት የተነሣ ቅጥር እንደሌላቸው መንደሮች ሆና ትኖራለች። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 ሩጥ፥ ይህንም ጕልማሳ እንዲህ በለው፦ ኢየሩሳሌም በውስጥዋ ካሉት ሰዎችና እንስሶች ብዛት የተነሣ ቅጥር እንደሌላቸው መንደሮች ሆና ትኖራለች። ምዕራፉን ተመልከት |