Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘካርያስ 2:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ዐይኖቼንም አንሥቼ እነሆም አራት ቀንዶች አየሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ደግሞም ወደ ላይ ተመለከትሁ፤ እነሆ፤ በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ ሰውም በፊቴ አየሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በሌላም ራእይ በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ አንድ ሰው አየሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ዓይኖቼንም አነሣሁ፣ እነሆም፥ በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ አንድ ሰውን አየሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ዓይኖቼንም አነሣሁ፥ እነሆም፥ በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ አንድ ሰውን አየሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘካርያስ 2:1
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆ፥ ፍሙን በወናፍ የሚያናፋ ለሥራውም መሣሪያ የሚያወጣ አንጥረኛን የፈጠርኩ እኔ ነኝ፤ የሚያፈርሰውንም እንዲያጠፋ ፈጥሬአለሁ።


የመለኪያውም ገመድ ወደ ጋሬብ ኮረብታ በቀጥታ ወደ ፊት ይሄዳል፥ ከዚያም ወደ ጎዓም ይዞራል።


የሞዓብ ቀንድ ተቈረጠ ክንዱም ተሰበረ፥ ይላል ጌታ።


ወደዚያም አመጣኝ፥ እነሆ፥ መልኩ ናስ የመሰለ አንድ ሰው በዚያ ነበረ፥ በእጁም የተልባ እግር ገመድና የመለኪያ ዘንግ ይዞ ነበረ፤ እርሱም በበሩ አጠገብ ቆሞ ነበር።


እነሆ፥ በቤቱ ውጭ በዙሪያው ቅጥር ነበረ፥ በሰውዬውም እጅ ያለው የመለኪያው ዘንግ ርዝመት አንድ ክንድ ከስንዝር የሆነ ስድስት ክንድ ነበረ፤ ቅጥሩንም ለካ፥ ስፋቱ አንድ ዘንግ፥ ቁመቱም አንድ ዘንግ ነበር።


ሰውዬው ገመድ በእጁ ይዞ ወደ ምሥራቅ ወጣ፥ አንድ ሺህ ክንድ ለካ፥ በውኃውም ውስጥ አሳለፈኝ፥ ውኃውም እስከ ቁርጫምጭሚት ድረስ ነበር።


እንደገና አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሳለፈኝ፥ ውኃውም እስከ ጉልበት ድረስ ነበር። ደግሞም አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሳለፈኝ፥ ውኃውም እስከ ወገብ ድረስ ነበር።


ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ወደ ኢየሩሳሌም በምሕረት ተመልሻለሁ፤ ቤቴ መልሶ ይገነባባታል፤ በኢየሩሳሌምም ላይ መለኪያ ገመድ ይዘረጋበታል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


በትር የሚመስል የመለኪያ ሸንበቆ ተሰጠኝ፤ እንዲህም ተባልሁ “ተነሥተህ የእግዚአብሔርን መቅደስና መሠዊያውን በዚያም የሚሰግዱትን ለካ።


የተናገረኝም ከተማይቱንና ደጆችዋን ቅጥርዋንም ይለካ ዘንድ የወርቅ ዘንግ ነበረው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች