Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘካርያስ 14:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በኢየሩሳሌም ላይ ከመጡት ከአሕዛብ ሁሉ የቀሩት ሁሉ ለንጉሡ ለሠራዊት ጌታ ለመስገድ፥ የዳስ በዓልንም ለማክበር በየዓመቱ ይወጣሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከዚያም ኢየሩሳሌምን ከወጓት አሕዛብ ከሞት የተረፉት ሁሉ ለንጉሡ፣ ለሰራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ለመስገድና የዳስን በዓል ለማክበር በየዓመቱ ይወጣሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከዚያም በኋላ ኢየሩሳሌምን ከወጉአት መንግሥታት መካከል ከጥፋት የተረፉት ለንጉሡ ለሠራዊት አምላክ ሊሰግዱለትና የዳስ በዓልንም ለማክበር በየዓመቱ ወደ ኢየሩሳሌም ይወጣሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በኢየሩሳሌም ላይ ከመጡት ከአሕዛብ ሁሉ የቀሩት ሁሉ ለንጉሡ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ይሰግዱ ዘንድ፥ የዳስ በዓልንም ያከብሩ ዘንድ በየዓመቱ ይወጣሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በኢየሩሳሌም ላይ ከመጡት ከአሕዛብ ሁሉ የቀሩት ሁሉ ለንጉሡ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ይሰግዱ ዘንድ፥ የዳስ በዓልንም ያከብሩ ዘንድ በየዓመቱ ይወጣሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘካርያስ 14:16
42 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንዲህ ይሆናል፤ በየመባቻውና በየሰንበቱ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በፊቴ ለመስገድ ዘወትር ይመጣል፥ ይላል ጌታ።


እንዲህም ይሆናል፥ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፥ ጌታም እንደ ተናገረ፥ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም የሚተርፉ ይኖራሉ። ደግሞም ጌታ የጠራቸው ይገኛሉ።


በልብሱና በጭኑም ላይ “የነገሥታት ንጉሥና የጌታዎች ጌታ” የሚል ስም ተጽፎአል።


በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ከከተማይቱም ዐሥረኛው እጅ ወደቀ፤ በመናወጥም ሰባት ሺህ ሰዎች ተገደሉ፤ የቀሩትንም ፍርሃት ያዛቸው፤ ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ።


እንደዚሁም እስራኤል ሁሉ ይድናል፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ “አዳኝ ከጽዮን ይወጣል፤ ከያዕቆብም ክፋትን ያስወግዳል።


በኩራቱም ቅዱስ ከሆነ ብኮው ደግሞ ቅዱስ ነው፤ ሥሩም ቅዱስ ከሆነ ቅርንጫፎቹ ደግሞ ቅዱሳን ናቸው።


እንደዚሁም በአሁን ዘመን ደግሞ በጸጋ ተመርጠው የተረፉ አሉ።


የቀሩት ሰዎችና በስሜ የተጠሩት አሕዛብ ሁሉ ጌታን እንዲፈልጉ፥ ይላል ይህን የሚያደርግ ጌታ።


የአይሁድም የዳስ በዓል ቀርቦ ነበር።


ናትናኤልም መልሶ “መምህር ሆይ! አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ” አለው።


እንዲህም አሉ፦ “በጌታ ስም የሚመጣ ንጉሥ የተባረከ ነው፤ በሰማይ ሰላም በአርያምም ክብር፥” አሉ።


“በመንጋው ውስጥ ተባዕት እያለው ለጌታ ተስሎት እያለ ነውር ያለበትን የሚሠዋ ተንኮለኛ ሰው የተረገመ ነው። እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፥ “ስሜም በሕዝቦች መካከል የተፈራ ነውና።”


ደሙንም ከአፉ ውስጥ፥ ርኩሱንም ነገር ከጥርሱ መካከል አስወግዳለሁ፤ እርሱም ደግሞ ለአምላካችን ቀሪ ሕዝብ ይሆናል፥ በይሁዳም እንደ አለቃ ይሆናል፥ አቃሮንም እንደ ኢያቡሳዊ ይሆናል።


ኤፍሬምም፦ “በእውነት ባለ ጠጋ ሆኜአለሁ፥ ሀብትንም አግኝቻለሁ፥ በድካሜም ሁሉ ኃጢአት የሚሆን በደል አያገኙብኝም” አለ።


አለቆችዋንና ጥበበኞችዋንም፥ ገዢዎችዋንና ሹማምቶችዋን ኃያላኖችዋንም አሰክራለሁ፥ ለዘለዓለምም አንቀላፍተው አይነቁም፥ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ የተባለው ንጉሥ።


ወደ ሞአብና ከተሞችዋ አጥፊው ወጥቶአል፥ የተመረጡትም ጉልማሶች ወደ መታረድ ወርደዋል፥ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ የሆነ ንጉሥ።


እኔ ሕያው በመሆኔ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ የተባለው ንጉሥ፥ በተራሮች መካከል እንዳለ እንደ ታቦር፥ በባሕርም አጠገብ እንዳለ እንደ ቀርሜሎስ፥ እንዲሁ በእውነት ይመጣል።


እኔም፤ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይቷልና ጠፍቻለሁ፤ ወዮልኝ!” አልሁ።


እንደተጻፈውም የዳስ በዓል አከበሩ፤ እንደ ሥርዓቱም የዕለቱን የሚቃጠል መሥዋዕት በዕለቱ በቍጥር አቀረቡ፤ የዕለቱን ነገር በዕለቱ።


ሙሴም እንዳዘዘ እንደ ሥርዓታቸው ዘወትር በየቀኑ፥ በየሰንበታቱም፥ በየመባቻዎቹም፥ በየተወሰኑትም በዓላት፥ በየዓመቱ ሦስት ጊዜ በየቂጣው በዓልና በየሰባቱ ሱባዔ በዓል በየዳሱም በዓል ቁርባን ያቀርቡ ነበር።


በምድር ያሉ ሁሉ ለአንተ ይሰግዳሉ፥ ለአንተም ይዘምራሉ፥ ለስምህም ይዘምራሉ።”


በዚያን ጊዜ ለሠራዊት ጌታ፥ ከረጅምና ከለስላሳ ሕዝብ፥ ከቅርብም ከሩቅም አስፈሪ ከሆነ ሕዝብ፥ ኀያል ከሆነና ከሚገዛ፥ ወንዞችም ምድራቸውን ከሚከፍሉት ሕዝብ ዘንድ ስጦታ ይመጣለታል፤ ስጦታውም የሠራዊት ጌታ ስም ወደሚገኝበት ወደ ጽዮን ተራራ ይቀርባል።


በዚያም ቀን ጌታ ለግብጻዊያን ራሱን ይገልጣል፤ ግብጻውያንም ጌታን ያውቃሉ፤ በመሥዋዕትና በእህል ቁርባንም ያመልኩታል፤ ለጌታም ስእለት ይሳላሉ፤ የተሳሉትንም ይፈጽማሉ።


በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ታላቅ መለከት ይነፋል፥ በአሦርም የጠፉ፥ በግብጽ ምድርም የተሰደዱ ይመጣሉ፤ በተቀደሰውም ተራራ በኢየሩሳሌም ለጌታ ይሰግዳሉ።


ብዙዎች አሕዛብ መጥተው፦ ኑ ወደ ጌታ ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ እኛም በፍለጋው እንሄዳለን ይላሉ፤ ከጽዮን ሕግ፥ ከኢየሩሳሌምም የጌታ ቃል ይወጣልና።


ጌታም በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፤ በዚያ ቀን ጌታ አንድ፥ ስሙም አንድ ይሆናል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች