ዘካርያስ 11:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 እኔም፦ “እናንተን አልጠብቅም፤ የሚሞተው ይሙት፥ የሚጠፋውም ይጥፋ፤ የቀሩትም እርስ በእርሳቸው ተበላልተው ይጨራረሱ።” አልሁ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 “እረኛችሁ አልሆንም፤ የሚሞቱት ይሙቱ፤ የሚጠፉት ይጥፉ፤ የቀሩትም አንዱ የሌላውን ሥጋ ይብላ” አልኋቸው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ከዚህ በኋላ መንጋውን እንዲህ አልኩ፦ “እኔ ከእንግዲህ ወዲህ እረኛችሁ አልሆንም፤ የሚሞቱት ይሙቱ፤ የሚጠፉትም ይጥፉ፤ የተረፉትም እርስ በርሳቸው ተባልተው ይለቁ፤” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 እኔም፦ እናንተን አልጠብቅም፣ የሚሞተው ይሙት፥ የሚጠፋውም ይጥፋ፣ የቀረውም እያንዳንዱ የባልንጀራውን ሥጋ ይብላ አልሁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 እኔም፦ እናንተን አልጠብቅም፥ የሚሞተው ይሙት፥ የሚጠፋውም ይጥፋ፥ የቀረውም እያንዳንዱ የባልንጀራውን ሥጋ ይብላ አልሁ። ምዕራፉን ተመልከት |