ዘካርያስ 11:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 የእረኞች ክብር ተዋርዶአልና የዋይታቸውን ድምፅ ስሙ! የዮርዳኖስ ጥቅጥቅ ደን ወድሟልና የአንበሶች ግሣት ድምፅ ስሙ! ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 የእረኞችን ዋይታ ስሙ፤ ክብራቸው ተገፍፏልና፤ የአንበሶችን ጩኸት ስሙ፤ ጥቅጥቅ ያለው የዮርዳኖስ ደን ወድሟል! ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 እረኞች ለምለም የሆነ መሰማሪያቸው ስለ ወደመ “ዋይ!” እያሉ ሲያለቅሱ ስሙ፤ የዮርዳኖስን ወንዝ ተከትሎ ያለው የደን መኖሪያቸው ስለ ተደመሰሰ፥ አንበሶች በሐዘን ሲያገሡ ስሙ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 የእረኞች ክብር ተዋርዶአልና የዋይታቸው ድምፅ ተሰምቶአል፣ የዮርዳኖስ ትዕቢት ተዋርዶአልና የአንበሶች ግሣት ድምፅ ተሰምቶአል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 የእረኞች ክብር ተዋርዶአልና የዋይታቸው ድምፅ ተሰምቶአል፥ የዮርዳኖስ ትዕቢት ተዋርዶአልና የአንበሶች ግሣት ድምፅ ተሰምቶአል። ምዕራፉን ተመልከት |