ዘካርያስ 10:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 እርሱም በጭንቅ ባሕር ያልፋል፥ የባሕር ሞገድም ጸጥ ያሰኛል፥ የዐባይም ወንዝ ከጥልቀት ይደርቃል። የአሦርም ትዕቢት ይዋረዳል፥ የግብጽም በትረ መንግሥት ይጠፋል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 በመከራ ባሕር ውስጥ ያልፋሉ፤ የባሕሩ ማዕበል ጸጥ ይላል፤ የአባይም ጥልቅ ሁሉ ይደርቃል። የአሦር ትምክሕት ይዋረዳል፤ የግብጽም በትረ መንግሥት ያበቃል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 በመከራ ባሕር ውስጥ ሲያልፉ እኔ እግዚአብሔር ማዕበሉን እመታለሁ፤ ጥልቅ የሆነውም የዓባይ ወንዝ ይደርቃል፤ ትዕቢተኛይቱ አሦር ትዋረዳለች፤ ግብጽም በትረ መንግሥትዋን ታጣለች። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 እርሱም በጭንቅ ባሕር ያልፋል፥ የባሕርንም ሞገድ ይመታል፥ የወንዙም ጥልቅ ሁሉ ይደርቃል፣ የአሦርም ትዕቢት ይዋረዳል፥ የግብጽም በትረ መንግሥት ይርቃል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 እርሱም በጭንቅ ባሕር ያልፋል፥ የባሕርንም ሞገድ ይመታል፥ የወንዙም ጥልቅ ሁሉ ይደርቃል፥ የአሦርም ትዕቢት ይዋረዳል፥ የግብጽም በትረ መንግሥት ይርቃል። ምዕራፉን ተመልከት |