ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጥበብ 7:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 እንደተወለድሁ እኔም አየር ስቤያለሁ፥ ሁላችንን በተሸከመችውም ምድር ላይ ወድቄያለሁ፤ እንደ ሌሎች ሁሉ የመጀመሪያው ድምፄም ለቅሶ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 በተፈጠርሁም ጊዜ እንደ ሰው ሁሉ ነፍስን ነሣሁ፥ በመከራዬም ምሳሌ ወደ ምድር ወረድሁ፤ የቃልም መጀመርያ እንደ ሁሉ ልቅሶን አለቀስሁ። ምዕራፉን ተመልከት |