ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጥበብ 6:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 የጥበብን ምንነትና አፈጣጠር ቀጥዬ አብራራለሁ፤ ምንም ምሥጢር አልደብቃችሁም፤ ከተፈጠረችበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን ዕድገቷን እገልጻለሁ፤ ስለ እርሷ የምናውቀውን ሁሉ ይፋ አደርጋለሁ፤ ከእውነት ግን አልርቅም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ጥበብ ምንድን ናት? እንደ ምንስ ነበረች? እኔ እነግራችኋለሁ፤ የተሰወረ ምሥጢሯንም ከእናንተ አልሰውርም። ነገር ግን ከጥንት ጀምሮ አኳኋኗን እመረምራለሁ፤ እርሷን ማወቅንም የተገለጠ አደርጋለሁ፤ እውነትንም አልተላለፍም። ምዕራፉን ተመልከት |