ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጥበብ 4:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ፈጥነውም ክብሩን ያጣ ሬሳ ይሆናሉ፤ በሙታንም መካከል ዘላለማዊ ማስፈራርያ ይሆናሉ። እርሱ ይሰባብራቸዋል፤ በጭንቅላታቸው ያሽቀነጥራቸዋል፤ እነርሱም ይደነዝዛሉ። ከመሠረታቸው ያናጋቸዋል፤ ወና ይሆናሉ፤ ኀዘን ይነግሥባቸዋል፤ መታሰቢያቸውም ሁሉ ይጠፋል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ከዚህም በኋላ ለጐስቋላ ሞት ይሆናሉ፤ ለዘለዓለምም ሙታን ለሚሰደቡበት ስድብ ይሆናሉ። ይቈርጣቸዋልና፥ ይሰነጥቃቸዋልምና፥ ቃልም ሳይኖራቸው በፊታቸው የወደቁ ሆነው ይገኛሉ። ከመሠረታቸውም ያነዋውጣቸዋል፤ ለዘለዓለሙ እንደ ተፈታች ምድር ይሆናሉ፥ የተጨነቁም ይሆናሉ፤ መታሰቢያቸውም ይጠፋል። ምዕራፉን ተመልከት |