ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጥበብ 13:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 እግዚአብሔርን የማያውቁ ሁሉ፥ በእውነት በባሕርያቸው ከንቱ ናቸው፤ ከሚታዩት መልካም ነገሮች፥ እርሱ የሆነውን ወደ ማወቅ አልደረሱም፤ አልያም የእጁን ሥራዎች በመመልከት፥ ሠሪውን ማስተዋል አልቻሉም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 እግዚአብሔርን የማወቅ ጕድለት በልቡናቸው ያለባቸው ሰዎች ሁሉ በእውነት ከንቱ ናቸውና፥ በሚታዩ መልካም ነገሮች ያለውን ያውቁ ዘንድ ተሳናቸው፥ ሥራውንም እያዩ ሠሪውን አላወቁትም። ምዕራፉን ተመልከት |