ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጦቢት 6:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ጦብያ ለሩፋኤል እንዲህ ሲል መለሰለት፥ “ወንድሜ አዛርያ እስዋ ከዚህ ቀደም ሰባት ጊዜ ባል እንዳገባችና ሰባቱም ባሎችዋ በሰርጉ ቀን ወዳለችበት ጫጉላ ሲገቡ እንደሞቱ ሰምቻለሁ። ወደ እርሷ በገቡበት በዚያች ሌሊት ይሞታሉ። የገደላቸውም አንድ ጋኔን መሆኑን ሰምቻለሁ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 አሁንም እኔ ላባቴ ብቸኛ ነኝ፤ ወደ እርሷም በገባሁ ጊዜ እንዳልሞት ፥ ያባቴንና የናቴንም ሕይወት በእኔ ምክንያት በጭንቅ ወደ መቃብር እንዳላወርድ እፈራለሁ፤ የሚቀብራቸውም ሌላ ልጅ የላቸውምና።” ምዕራፉን ተመልከት |