ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጦቢት 6:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 አንተ እርሷን ለማግባት መብት አለህ፥ ስማኝ ወንድሜ፥ ይህች ልጃገረድ ያንተ እጮኛ እንድትሆን ዛሬውኑ ለአባትዋ እኔ እናገራለሁ፥ ከራጌስ ስንመለስ ሰርጉን እንደግሳለን፥ ራጉኤል አንተን ከልክሎ ለሌላ ሊድራት እንደማይችል አረጋግጥልሃልሁ፥ ምክንያቱም ልጅቷን ላንተ መዳር እንደሚገባው እያወቀ ለሌላ ሰው ቢድራት በሙሴ መጽሐፍ መሠረት በሞት ይቀጣል። ስለዚህ ወንድሜ ምክሬን ስማ፥ ዛሬ ማታ ስለ ልጅቷ ተነጋግረን ለጋብቻ እንጠይቃታለን፥ ከራጌስ ስንመለስ ከእኛ ጋር ወደ ቤት ይዘናት እንሄዳለን።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 ያም ልጅ መልአኩን አለው፥ “አንተ ወንድሜ አዛርያ! ያቺን ልጅ ለሰባት ወንዶች እንዳጋቧት እኔ ሰምቻለሁ፤ ሁሉም በሠርጉ ጊዜ ሞቱ። ምዕራፉን ተመልከት |