ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጦቢት 5:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 መልአኩ ወደ ቤት ገባ፤ ጦቢትም አስቀድሞ ሰላምታ ሰጠው፤ እርሱም “መልካም ነገር እመኝልሃለሁ” ሲል መለሰለት። ጦቢትም “ከእንግዲህ ወዲህ ምን መልካም ነገር ማግኘት እችላለሁ? ዐይኖቼን አጥቻለሁ፤ የሰማይን ብርሃን ማየት አልችልም፥ ብርሃንን እንደማያዩ ሙታን በጨለማ እገኛለሁ፥ ሕያው ብሆንም ከሞቱት ጋር እቆጠራለሁ፥ ሰዎች ሲናገሩ ድምፃቸውን እሰማለሁ ነገር ግን አላያቸውም” አለ፤ መልአኩም “አይዞህ፥ በቅርቡ እግዚአብሔር ይፈውስሃል፤ አይዞህ” አለው። ጦቢትም “ልጄ ጦብያ ወደ ሜዶን መሄድ ይፈልጋል፤ የመንገድ ጓደኛው በመሆን ልትመራው ትችላለህን? ደሞዝህን እከፍልሃለሁ ወንድሜ።” አለው። እሱም “ከእርሱ ጋር እሄዳለሁ፤ መንገዶቹን ሁሉ አውቃቸዋለሁ፥ ወደ ሜዶን ብዙ ጊዜ ሄጄአለሁ፤ በሜዳዎቹና በተራራዎቹም አቋርጫለሁ፥ መንገዶቹንም ሁሉ አውቃቸዋለሁ” አለው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ጦቢትም፥ “አንተ ወንድሜ! ከማን ወገን ነህ? ከወዴትስ ሀገር ነህ?” አለው። ምዕራፉን ተመልከት |