ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጦቢት 3:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 አሁንም እንደ ፈቀድህ አድርገኝ፤ ከዚህች ምድር ተላቅቄ ዳግም አፈር ልሁን፥ ከመኖር መሞት ይሻለኛልና፥ ከንቱ ስድብን ተቋቁሜአልሁና፥ በታላቅ ኃዘንም ውስጥ ነኝ፤ ጌታ ሆይ ከዚህ መከራ እንድላቀቅ እዘዝ፥ ወደ ዘላለማዊ ቤቴም እንድሄድ ፍቀድ፤ ጌታ ሆይ ፊትህን ከኔ አትመልስ፤ በማያባራ ሰቆቃ ከተሞላ ሕይወት ይልቅ ሞቴን እመርጣለሁ፥ ከዚህ ወዲያ ስድቦችን መሸከም አልችልም።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 አሁንም በፊትህ ደስ የሚያሰኝህን በእኔ አድርግ፤ ከመኖር መሞት ይሻለኛልና በሞት እሰናበት ዘንድ፥ መሬትም እሆን ዘንድ ነፍሴን የሚቀበላትን እዘዝልኝ። በሐሰትና በውርደት ተግዳሮትን ሰምቻለሁና፥ ኀዘንም በእኔ ላይ በዝትዋልና ከመከራዬ እሰናበት ዘንድ፥ ወደ ዘለዓለማዊ ቦታም እሄድ ዘንድ እዘዝ፤ ፊትህንም ከእኔ አትመልስ።” ምዕራፉን ተመልከት |