ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጦቢት 14:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 በጽድቅ የዘመናትን አምላክ ይባርካሉ። በእነዚህ ቀኖች የዳኑ እስራኤላውያን ከልባቸው እግዚአብሔርን ያስታውሱታል። ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣሉ ይሰበሰባሉም፥ ከዛ በኋላም የእነሱ በምትሆን በአብርሃም ምድር ላይ ያለ ሥጋት ይኖራሉ። ከልባቸው እግዚአብሔርን የሚወዱ ደስ ይላቸዋል፤ ኃጢአትንና ክፋትን የሚያደርጉ ግን ከምድር ይጠፋሉ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 አሕዛብ ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል። ሕዝቡም በእርሱ ያምናሉ፤ እግዚአብሔርም ወገኖቹን ከፍ ከፍ ያደርጋቸዋል። በእውነትና በቅንነት እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ሁሉ ደስ ይላቸዋል፤ ለወንድሞቻቸውም ቸርነትን ያደርጋሉ። ምዕራፉን ተመልከት |