ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጦቢት 14:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንደገና ይራራላቸዋል፥ ወደ እስራኤል ምድርም ይመልሳቸዋል፤ እንደ በፊቱ ቆንጆ ባይሆንም ዘመኑ እስኪፈጸም ድረስ ቤቱን እንደገና ያንጻሉ፥ ከዚህ በኋላ ግን ሁሉም ከምርኮ ተመለሰው ይመጣሉ፥ ኢየሩሳሌምን ከነሙሉ ክብርዋ እንደገና ያንጽዋታል። የእግዚአብሔርም ቤት የእስራኤል ነቢያት እንደ ተነበዩት በውስጧ እንደገና ይታነጻል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ዳግመኛም እግዝአብሔር ይቅር ብሎ ወደ ሀገራቸው ይመልሳቸዋል፤ ማደሪያው ቤተ መቅደስንም ይሠራሉ፤ የዘመኑ ቍጥር እስከሚፈጸም ነው እንጂ እንደ ቀድሞው አይደለም፤ ከዚህም በኋላ ከተማረኩበት ይመለሳሉ፤ ኢየሩሳሌምንም በክብር ይሠሯታል፤ በእርሷም የእግዚአብሔርን ቤት እስከ ልጅ ልጅ ዘመን ድረስ በዕብነ በረድ ይሠራሉ። ምዕራፉን ተመልከት |