ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጦቢት 11:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ጦቢት ደስ ብሎት እግዚአብሔርን እያመሰገነ የልጁን ሚስት ለመቀበል ወደ ነነዌ በር ወጣ። የነነዌ ሰዎች ጦቢትን ማንም ሳይመራው ሲራመድና ሲዘዋዋር ባዩት ጊዜ ተደነቁ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ጦቢት ግን በፊታቸው እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ እግዚአብሔር ይቅር ብሎታልና። ጦቢትም ወደ ምራቱ ወደ ሣራ በደረሰ ጊዜ፥ “ልጄ! እንኳን በደኅና ገባሽ!” ብሎ መረቃት፤ ወደ እኛ ያመጣሽ እግዚአብሔርም ይመስገን፤ አባትሽንና እናትሽንም ይባርክ” አላት። በነነዌም ለሚኖሩ ለወንድሞቹ ሁሉ ታላቅ ደስታ ሆነ። ምዕራፉን ተመልከት |