ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ሲራክ 23:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ሁልጊዜ የሚምል ሰው በኃጢአት የተሞላ ነው፤ ምንጊዜም ከቤቱ መቅሠፍት አይጠፋም። እርሱ ከበደለ ኃጢአቱ በራሱ ላይ ይወድቃል፤ ካለመጠንቀቅ የፈጸመው ከሆነ ደግሞ፤ ኃጢአቱ ድርብ ይሆንበታል። በሐሰት ከማለ ይቅርታ አይደረግለትም፤ ቤቱም በመቅሠፍት ይሞላል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 መሐላን የሚያበዛ ሰው ኀጢአቱ ብዙ ነው፥ ከቤቱም መቅሠፍት አይርቅም፤ ቢያረጅም ኀጢአቱ አይተወውም፤ ቸል ቢልም ኀጢአቱ እጥፍ ይሆንበታል፤ ፍዳው በቤቱ ሞልትዋልና ስለ ማለ እውነተኛ አይባልም። ምዕራፉን ተመልከት |