Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሩት 1:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 መሐሎንና ኬሌዎን ሁለቱም ሞቱ፥ ሴቲቱም ሁለቱን ልጆችዋንና ባልዋን አጥታ ብቻዋን ቀረች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 መሐሎንና ኬሌዎን ሁለቱም ሞቱ፤ ኑኃሚንም ሁለት ልጆቿንና ባሏን ዐጥታ ብቻዋን ቀረች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ማሕሎንና ኬሌዎንም ሞቱ፤ ናዖሚም ባልዋንና ልጆችዋን አጥታ ብቻዋን ቀረች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 መሐሎንና ኬሌዎንም ሁለቱ ሞቱ፣ ሴቲቱም ከሁለቱ ልጆችዋና ከባልዋ ተለይታ ቀረች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 መሐሎንና ኬሌዎንም ሁለቱ ሞቱ፤ ሴቲቱም ከሁለቱ ልጆችዋና ከባልዋ ተለይታ ቀረች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሩት 1:5
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንቺም በልብሽ፦ “የወላድ መካን ሆኛለሁና፥ እኔም ብቻዬን ተሰድጄአለሁ፥ ተቅበዝብዤአለሁ፥ እነዚህን ማን ወለደልኝ? እነዚህንስ ማን አሳደጋቸው? እነሆ፥ ብቻዬን ቀርቼ ነበር፤ እነዚህስ ወዴት ነበሩ?” ትያለሽ።


ክፋትሽ ይቀጣሻል ክህደትሽ ይገሥጽሻል፤ ጌታን አምላክሽን መተውሽ ምን ያኽል ክፉና መራራ ነገር እንደሆነ እወቂም፥ ተመልከቺም፤ እኔን መፍራት በአንቺ ውስጥ የለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ወደ ከተማይቱም በር በቀረበ ጊዜ፥ እነሆ፥ አንድ የሞተ ሰው ተሸክመው እያወጡ ነበር፤ እርሱም ለእናቱ አንድ ነበረ፤ እርሷም መበለት ነበረች፤ የከተማይቱም ብዙ ሕዝብ ከእርሷ ጋር አብረው ነበሩ።


“እኔ ራሴ እርሱ እንደሆንሁ እዩ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እኔ እገድላለሁ፤ በሕይወትም አኖራለሁ፤ እኔ አቆስላለሁ፤ እፈውሳለሁም፤ ከእጄም የሚያስጥል ማንም የለም።


የሰውዬው ስም ኤሊሜሌክ፥ የሚስቱም ስም ናዖሚ፥ የሁለቱም ልጆች ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበረ፥ እነርሱም የቤተልሔም ይሁዳም የኤፍራታ ሰዎች ነበሩ። ወደ ሞዓብም ምድር መጡ፥ በዚያም ተቀመጡ።


እነርሱም ከሞዓባውያን ሴቶች ሚስት አገቡ፥ የአንዲቱ ስም ዖርፋ የሁለተኛይቱም ስም ሩት ነበረ። በዚያም ዐሥር ዓመት ያህል ተቀመጡ።


እርሷም በሞዓብ ምድር ሳለች ጌታም ሕዝቡን እንደ ጐበኘ እህልም እንደሰጣቸው ስለ ሰማች፥ ከሞዓብ ምድር ልትመለስ ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ተነሣች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች