Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሮሜ 9:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እንግዲህ የፈለገውን ይምረዋል የፈለገውንም እልከኛ ያደርገዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ስለዚህ እግዚአብሔር ሊምረው ለሚወድደው ምሕረት ያደርግለታል፤ ልቡ እንዲደነድን የፈለገውንም ያደነድነዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ስለዚህ እግዚአብሔር የሚፈልገውን ይምረዋል፤ የሚፈልገውንም እልኸኛ ያደርገዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እነሆ፥ የሚ​ወ​ድ​ደ​ውን ይም​ረ​ዋል፤ የሚ​ወ​ድ​ደ​ው​ንም ልቡን ያጸ​ና​ዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እንግዲህ የሚወደውን ይምረዋል፥ የሚወደውንም እልከኛ ያደርገዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሮሜ 9:18
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ ሙሴን እንዳዘዘ፥ እንዲያጠፉአቸው ምሕረትንም ሳያደርጉ ፈጽመው እንዲፈጅዋቸው፥ ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት ልባቸውን እንዲያደነድኑ ከጌታ ዘንድ ሆነ።


ጌታም ሙሴን አለው፦ “ወደ ግብጽ ስትመለስ በእጅህ ያደረግሁትን ተአምራት ሁሉ ተመልከት በፈርዖንም ፊት ታደርጋቸዋለህ፤ እኔም ልቡን አጸናዋለሁ፥ ሕዝቡንም አይለቅቅም።


“የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም፥ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጅህ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ፥ ጌታ አምላካችሁ መንፈሱን አደንድኖታልና ልቡንም አጽንቶታልና።”


አቤቱ ጌታ፥ ከመንገድህ ለምን አሳትኸን? እንዳንፈራህም ልባችንን ለምን አጸናህብን? ስለ አገልጋዮችህ ስትል ስለ ርስትህ ነገዶች ተመለስ።


ልክ ጌታ እንደ ተናገረው የፈርዖን ልብ ጸና፥ አልሰማቸውምም።


በውድ ልጁም በነጻ የሰጠን የከበረ ጸጋው እንዲመሰገን ይህን አደረገ።


እኔም የፈርዖንን ልብ አደነድናለሁ፥ ምልክቶቼንና ድንቆቼን በግብጽ ምድር ላይ አበዛለሁ።


ጌታም የፈርዖንን ልብ አጸና፤ ጌታ ሙሴን እንደ ተናገረው ፈርዖን አልሰማቸውም።


ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደ ፈርዖን ግባ እኔ ልቡንና የአገልጋዮቹን ልብ ያደነደንኩት በመካከላቸው ምልክቶቼን እንዳሳይ ነው።


ጌታም የፈርዖንን ልብ አጸና የእስራኤልንም ልጆች አልለቀቀም።


ጌታ ግን የፈርዖንን ልብ አጸና፥ ሊለቅቃቸውም አልወደደም።


ሙሴና አሮንም እነዚህን ተአምራቶች ሁሉ በፈርዖን ፊት አደረጉ፤ ጌታም የፈርዖንን ልብ አጸና፥ የእስራኤልንም ልጆች ከአገሩ አልለቀቀም።


እኔም የፈርዖንን ልብ አጸናለሁ፥ እርሱም ያሳድዳቸዋል፤ በፈርዖንና በሠራዊቱም ሁሉ ላይ ክብር አገኛለሁ፤ ግብፃውያንም እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ። እነርሱም እንዲሁ አደረጉ።


እነሆ እኔ የግብፃውያንን ልብ አጸናለሁ፥ ከኋላቸውም ይገባሉ፤ በፈርዖንና በሠራዊቱም ሁሉ በሰረገሎቹም በፈረሰኞቹም ላይ ክብር አገኛለሁ።


“በዐይኖቻቸው እንዳያዩ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ እንዳይመለሱም፥ እኔም እንዳልፈውሳቸው፥ ዐኖቻቸውን አሳወረ፤ ልባቸውውንም አደነደነ።”


ወንድሞች ሆይ! አላዋቂዎች እንድትሆኑ አልፈልግም፤ ይህን ምሥጢር እንድታውቁ እወዳለሁ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ እስራኤል በከፊል መደንዘዝ ሆነበት፤


ፈርዖንም ላከ፥ እነሆም ከእስራኤል ልጆች ከብት አንድ ስንኳ አልሞተም። የፈርዖን ልብ ግን ደነደነ፥ ሕዝቡንም አልለቀቀም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች