Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሮሜ 7:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ኃጢአት ግን በትእዛዝ አማካኝነት አጋጣሚን በመውሰድ ሁሉንም ዓይነት ምኞትን አስነሣ፤ ኃጢአት ያለ ሕግ የሞተ ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ኀጢአት ግን ትእዛዙ ባስገኘው ዕድል ተጠቅሞ በእኔ ውስጥ ማንኛውንም ዐይነት ዐጕል ምኞት አስነሣ፤ ኀጢአት ያለ ሕግ ምዉት ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ኃጢአት ከሕግ በመጣው ትእዛዝ ዕድል አግኝቶ ምኞትን ሁሉ በኔ ውስጥ እንዲቀሰቀስ አደረገ። ሕግ ከሌለ ግን ኃጢአት የሞተ ነገር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ያችም ትእ​ዛዝ ለኀ​ጢ​አት ምክ​ን​ያት ሆነ​ቻት፤ ምኞ​ት​ንም ሁሉ አመ​ጣ​ች​ብኝ፤ ቀድሞ ግን ኦሪት ሳት​ሠራ ኀጢ​አት ሙት ነበ​ረች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ኃጢአት ግን ምክንያት አግኝቶ ምኞትን ሁሉ በትእዛዝ ሠራብኝ፤ ኃጢአት ያለ ሕግ ምውት ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሮሜ 7:8
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኃጢአት በትእዛዝ በኩል አጋጣሚ አግኝቶ አታልሎኛልና፥ በእርሱም ገደለኝ።


የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው፤ የኃጢአትም ኃይል ሕግ ነው።


ሕጉ መቅሠፍትን ያስከትላልና፤ ነገር ግን ሕግ በሌለበት መተላለፍ የለም።


እንግዲህ መልካም የሆነው ነገር ሞት ሆነብኝን? በጭራሽ! ነገር ግን ኃጢአት ኃጢአትነቱ እንዲታይ፥ መልካም በሆነው ነገር ሞትን ይሠራብኝ ነበር። ይኸውም ኃጢአት በትእዛዝ አማካይነት ያለ ልክ ኃጢአት እንዲሆን ነው።


በደል እንዲበዛ ሕግ ገባ፤ ነገር ግን ኃጢአት በበዛበት፥ ጸጋ ይበልጥ በዛ፤


እኔ መጥቼ ባልነገራቸው ኖሮ ኃጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን ለኀጢአታቸው ሰበብ የላቸውም።


እንግዲህ አሁን ይህን የማደርገው እኔ ሳልሆን፥ በእኔ ውስጥ የሚያድረው ኃጢአት ነው።


ሌላ ሰው ያላደረገውን ሥራ በመካከላቸው ባላደርግ ኖሮ ኃጢአት ባልሆነባቸው ነበር፤ አሁን ግን እኔንም አባቴንም አይተዋል፤ ጠልተውማል።


መስገብገብ፥ ክፋት፥ ማታለል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስም ማጥፋት፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸው።


ምክንያቱም በሕግ ሥራ ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት አይጸድቅም፤ በሕግ አማካኝነት ኃጢአት ይታወቃልና።


እኔም ድሮ ያለ ሕግ ሕያው ነበርሁ፤ ትእዛዝ በመጣ ጊዜ ግን ኃጢአት ሕያው ሆነ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች