ሮሜ 7:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ወንድሞች ሆይ! ሕግን ለሚያውቁ እናገራለሁና፤ ሕግ ሰውን የሚገዛው በሕይወት እስካለ ድረስ ብቻ መሆኑን አታውቁምን? ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ወንድሞች ሆይ፤ ሕግን ለሚያውቁ ሰዎች እናገራለሁ፤ ሕግ በአንድ ሰው ላይ ሥልጣን የሚኖረው፣ ሰውየው በሕይወት እስካለ ድረስ ብቻ መሆኑን አታውቁምን? ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ወንድሞቼ ሆይ! ይህን አታውቁምን? የምናገረው ሕግን ለሚያውቁ ሰዎች ነው፤ ሕግ በሰው ላይ ሥልጣን የሚኖረው ሰው በሕይወት እስካለ ድረስ ብቻ ነው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ወንድሞቻችን! ሕግን ለሚያስተውሉ እናገራለሁና፤ ሰው በሕይወት ባለበት ሁሉ ሕግ እንዲገዛው አታውቁምን? ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ወንድሞች ሆይ፥ ሕግን ለሚያውቁ እናገራለሁና ሰው ባለበት ዘመን ሁሉ ሕግ እንዲገዛው አታውቁምን? ምዕራፉን ተመልከት |