Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሮሜ 6:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት ባርያዎች እንዳንሆን የኃጢአት ሰውነት እንዲሻር አሮጌው ማንነታችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ከእንግዲህ የኀጢአት ባሮች እንዳንሆን፣ የኀጢአት ሰውነት እንዲሻር አሮጌው ሰዋችን ከርሱ ጋራ እንደ ተሰቀለ እናውቃለን፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ኃጢአተኛው ሰውነታችን እንዲወገድና የኃጢአት ባሪያዎች መሆናችን እንዲቀር አሮጌው ሰውነታችን ከክርስቶስ ጋር መሰቀሉን እናውቃለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ነገር ግን የኀ​ጢ​አ​ትን ሥጋ ይሽር ዘንድ ከእ​ርሱ ጋር የተ​ሰ​ቀ​ለው አሮ​ጌው ሰው​ነ​ታ​ችን እንደ ሆነ ይህን እና​ው​ቃ​ለን፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ ዳግ​መና ለኀ​ጢ​አት እን​ገዛ ዘንድ አን​መ​ለ​ስም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሮሜ 6:6
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ክርስቶስ በእኔ ይኖራል እንጂ ከእንግዲህ ወዲያ እኔ አልኖርም፤ አሁን በሥጋ የምኖረው በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ በማመን የምኖረው ነው።


ስለ ቀድሞ አኗኗሯችሁም፥ በሚያታልል ምኞቱ የጎደፈውንና የተበላሸውን፥ አሮጌ ሰው አውልቃችሁ እንድትጥሉ ተምራችኋል፤


የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑት ሥጋን ከመሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቅለውታል።


ለእኔ ግን፥ ዓለም ለእኔ እኔም ለዓለም ከተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት አይሁንብኝ።


እንግዲህ በእናንተ ያሉትን ምድራዊ ነገሮች ሁሉ ግደሉ፤ እነርሱም፦ “ዝሙትና ርኩሰት ፍትወትም ክፉ ምኞትም ጣዖትንም ማምለክ የሆነ ስግብግብነት” ናቸው፤


እንደ ሥጋ ብትኖሩ ትሞታላችሁና የሰውነትን ሥራ በመንፈስ ብትገድሉ ግን በሕይወት ትኖራላችሁ።


አሁን ግን ከኃጢአት ነፃ ወጥታችሁ ለእግዚአብሔርም ባርያዎች ሆናችኋል፥ ፍሬያችሁም ቅድስና ነው፤ መጨረሻውም የዘለዓለም ሕይወት ነው።


ስለዚህ፥ ለምኞቱ ታዛዥ ሊያደርጋችሁ በሚሞተው ሰውነታችሁ ላይ ኃጢአት አይንገሥ።


አቤቱ አምላካችን ጌታ ሆይ፥ ከአንተ በቀር ሌሎች ጌቶች ገዝተውናል፤ ነገር ግን የአንተን ስም ብቻ እናስባለን።


ስለዚህም ንዕማን እንዲህ አለ፦ “ስጦታዬን የማትቀበለኝ ከሆነ ከአሁን ጀምሮ ለእግዚአብሔር ብቻ እንጂ ለሌሎች ባዕዳን አማልክት የሚቃጠልም ሆነ ወይም ሌላ ዓይነት መሥዋዕት ስለማላቀርብ የሁለት በቅሎ ጭነት ዐፈር ይዤ እንድሄድ ፍቀድልኝ፤


ሕግ መንፈሳዊ መሆኑን እናውቃለን፤ እኔ ግን ከኃጢአት በታች ልሆን የተሸጥሁ የሥጋ ነኝ።


አንዱ ስለ ሁሉ እንደ ሞተ እርግጠኞች በመሆናችን፥ የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል፤ ይህ በመሆኑም ሁሉ ሞተዋል።


እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባርያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት ጊዜያችንን የምናሳልፍ፥ የምንጠላ፥ እርስ በርሳችንም የምንጠላላ ነበርን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች