Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሮሜ 4:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አብርሃም በሥራ ጸድቆ ቢሆን የሚመካበት አለውና፤ በእግዚአብሔር ፊት ግን መመካት አይችልም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አብርሃም በሥራ ጸድቆ ቢሆን ኖሮ፣ የሚመካበት ነበረው፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት መመካት አይችልም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 አብርሃም የጸደቀው በሥራ ቢሆን ኖሮ፥ የሚመካበት ነገር ባገኘ ነበር፤ ይሁን እንጂ በእግዚአብሔር ፊት መመካት አይችልም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 አብ​ር​ሃም በሥ​ራው ጸድ​ቆስ ቢሆን ትም​ክ​ሕት በሆ​ነው ነበር፤ ነገር ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ አይ​ደ​ለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አብርሃም በሥራ ጸድቆ ቢሆን የሚመካበት አለውና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሮሜ 4:2
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህ፥ እንደተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ “የሚመካ በጌታ ይመካ፤”


ትምክህት የሚያስፈልግ ከሆነ፥ መድከሜን በሚያሳይ ነገር እመካለሁ።


በክርስቶስም በማመን በእምነት ላይ የተመሠረተውን የእግዚአብሔርን ጽድቅ እንጂ በሕግ ላይ የተመሠረተውን የራሴ ጽድቅ ሳይኖረኝ፥ በእርሱ እንድገኝ ነው፤


ማንም እንዳይመካ ከሥራ የመጣም አይደለም።


ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት የሆነው የተስፋ ቃል ለሚያምኑ እንዲሰጥ፥ መጽሐፍ ሁሉን ነገር ከኃጢአት በታች ደምድሞታል።


ወንጌልን ብሰብክ እንኳ ግዴታዬ ነውና የምመካበት የለኝም፤ ወንጌልን ባልሰብክ ወዮልኝ!


ሥጋን የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ።


በልብ ሳይሆን በውጫዊ ነገር ለሚመኩ፥ የምትመልሱላቸው መልስ እንዲኖራችሁ፥ በእኛ ልትመኩ ምክንያት ልንሰጣችሁ እንጂ በእናንተ ፊት መልሰን ራሳችንን ለማመስገን ፈልገን አይደለም።


እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ዘንድ በሆነ ነገር የምመካበት አለኝ።


ፈርዖንም አብራምን ጠርቶ አለው፦ ይህ ያደረግህብኝ ምንድነው? እርሷ ሚስትህ እንደ ሆነች ለምን አልገለጥህልኝም?


ነገር ግን በሚመኩበት ሥራ ከእኛ እኩል በአቻነት ለመቆጠር የሚፈልጉ ሰዎችን ምክንያት ለማሳጣት፥ አሁን የማደርገውን ወደፊትም እገፋበታለሁ።


አንተን እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልከውስ ምን አለህ? እንግዲህ የተቀበልክ ከሆንክ፥ እንዳልተቀበልክ የምትመካው ስለ ምንድነው?


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ግባ፥ በዚህ የሚያደርጉትንም ክፉውን ርኩሰት ተመልከት።


ኢያሱም ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘አባቶቻችሁ፥ የአብርሃምና የናኮር አባት ታራ፥ አስቀድመው በወንዝ ማዶ ተቀመጡ፤ ሌሎችንም አማልክት አመለኩ።


ፈርዖንም ሰዎቹን ስለ እርሱ አዘዘ፥ እርሱንም ሚስቱንም ከብቱንም ሁሉ ሸኙአቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች