Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሮሜ 4:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ከሕግ የሆኑትስ ወራሾች ከሆኑ እምነት ከንቱ ሆኖአል፤ የተስፋውም ቃል ተሽሮአል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በሕግ የሚኖሩት ወራሾች ከሆኑ፣ እምነት የማይጠቅም፣ ተስፋም ከንቱ በሆነ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የተስፋው ወራሾች ሕግን የሚፈጽሙ ሰዎች ከሆኑማ እምነት ዋጋ አይኖረውም፤ ተስፋም ከንቱ መሆኑ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የኦ​ሪ​ትን ሕግ የፈ​ጸመ ብቻ ተስፋ የሚ​ያ​ገኝ፥ ዓለ​ም​ንም የሚ​ወ​ርስ ቢሆን ኖሮ፥ ለአ​ብ​ር​ሃም እም​ነቱ ባል​ጠ​ቀ​መ​ውም ነበር፤ ተስ​ፋ​ው​ንም ባላ​ገ​ኘም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ከሕግ የሆኑትስ ወራሾች ከሆኑ እምነት ከንቱ ሆኖአል የተስፋውም ቃል ተሽሮአል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሮሜ 4:14
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በክርስቶስም በማመን በእምነት ላይ የተመሠረተውን የእግዚአብሔርን ጽድቅ እንጂ በሕግ ላይ የተመሠረተውን የራሴ ጽድቅ ሳይኖረኝ፥ በእርሱ እንድገኝ ነው፤


ሕጉ ሰዎችን ድካም እያላቸው ሊቀ ካህናት አድርጎ ይሾማል፤ ከሕግ በኋላ የመጣ የመሐላው ቃል ግን፥ ለዘላለም ፍጹም የሆነውን ልጅ ሾመልን።


ሕጉ ምንም ፍጹም አላደረገምና፤ ወደ እግዚአብሔርም የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ ተዋውቀናል።


የእግዚአብሔርን ጸጋ አልናቅሁም፤ ጽድቅ በሕግ በኩል የሚገኝ ከሆነ እንግዲያውስ ክርስቶስ የሞተው በከንቱ ነው ማለት ነዋ!


ስለዚህ በእምነት የሆነው፥ ተስፋው በእምነት እንዲያርፍና ለዘሩ ሁሉ እንዲሆን ነው፥ ይህም ሕግ ፈፃሚዎች ብቻ ሳይሆኑ የአብርሃምን እምነት የሚጋሩትንም ጭምር ነው፥ እርሱ የሁላችንም አባት ነውና፥


ስለዚህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? በጭራሽ! ነገር ግን ሕግን እናጸናለን።


ከአፌ የሚወጣ ቃል እንዲሁ ይሆናል፤ የምሻውን ያደርጋል፤ የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም።


በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችኋል፥ ከጸጋውም ወድቃችኋል።


በዚህም ስፍራ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምክር አፈርሳለሁ፥ በጠላቶቻቸውም ፊት በሰይፍና ነፍሳቸውን በሚሹት እጅ እጥላቸዋለሁ፥ ሬሳቸውንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል አድርጌ እሰጣለሁ።


ለጌታ የሥራ ጊዜ ነው፥ ሕግህንም ሻሩት።


ዳሩ ግን ነገሩን ከሰማ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከንቱ ቢያደርገው በደልዋን ይሸከማል።


ባልዋ ግን በሰማበት ቀን ከንቱ ቢያደርገው፥ ስለ ስእለትዋ ወይም ራስዋን ስላሰረችበት መሐላ በአንደበትዋ የተናገረችው ማናቸውም ነገር አይጸናም፤ ባልዋ ከንቱ አድርጎታል፤ ጌታም ይቅር ይላታል።


ክርስቶስ ተከፍሎአልን? ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቅሎአልን? ወይስ የተጠመቃችሁት በጳውሎስ ስም ነበር?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች