Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሮሜ 3:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ ያቀረበው ነው፤ ይህም በእግዚአብሔር ትዕግስት በፊት የተደረገውን ኃጢአት በመተው ጽድቁን እንዲያሳይ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 በደሙም በሆነው እምነት፣ እግዚአብሔር የማስተሰረያ መሥዋዕት አድርጎ አቅርቦታል፤ ይህንም ያደረገው ቀድሞ የተፈጸመውን ኀጢአት ሳይቀጣ በትዕግሥት በማለፍ ጽድቁን ለማሳየት ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ በደሙ የኃጢአታቸውን ስርየት እንዲያገኙ ነው፤ እግዚአብሔር ይህን ማድረጉ በትዕግሥቱ የቀድሞውን ኃጢአት እንዳልነበረ በማድረግ የራሱን ትክክለኛ ፍርድ ለመግለጥ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 እር​ሱ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ም​ነት የሚ​ገኝ፥ በደ​ሙም የሆነ ማስ​ተ​ስ​ረያ አድ​ርጎ አቆ​መው፤ ይህም ከጥ​ንት ጀምሮ በበ​ደ​ሉት ላይ ጽድ​ቁን ይገ​ልጥ ዘንድ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሮሜ 3:25
51 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፍቅር በዚህ ነው፥ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው ሳይሆን ነገር ግን እርሱ እንደ ወደደን እና ለኃጢአታችንም ማስተስሪያ እንዲሆን ልጁን ስለላከልን ነው።


እርሱም የኃጢአታችን ማስተስረያ ነው፥ ለእኛ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ።


እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን ይበልጡንም በእርሱ በኩል ከቁጣ እንድናለን።


እንግዲህ እግዚአብሔር ያለማወቅን ወራት አሳልፎ አሁን በየቦታቸው ንስሓ ይገቡ ዘንድ ሰውን ሁሉ ያዛል፤


የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን ለማስወገድ አይችልም።


ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ የሕይወት መጽሐፍ ስሞቻቸው ያልተጻፉ የምድር ነዋሪዎች በሙሉ ይሰግዱለታል።


ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተ ስዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ፤ በዚህም ዓለምን ኰነነ፤ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።


ትውልድ ይገዛለታል፥ የሚመጣው ትውልድ ስለ ጌታ ይነገረዋል፥


“ለሕዝቡም የሆነውን የኃጢአት መሥዋዕት ፍየል ያርዳል፥ ደሙንም ወደ መጋረጃው ውስጥ ያመጣዋል፤ በወይፈኑም ደም እንዳደረገ እንዲሁ በፍየሉ ደም ላይ ያደርጋል፤ በስርየቱ መክደኛም ላይና በስርየቱ መክደኛም ፊት ለፈት ይረጨዋል።


እንግዲህ በእምነት ስለጸደቅን፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም አለን፤


በሕይወትም መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘው ሁሉ በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣለ።


“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።


እንደዚህ የሚሉት ሰዎች የራሳቸው የሆነውን አገር እንደሚጠባበቁ ያመለክታሉ።


ጽድቅህ የዘለዓለም ጽድቅ ነው፥ ቃልህም እውነት ነው።


ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም።


አብርሃም በተፈተነ ጊዜ ይስሐቅን በእምነት አቀረበ፤ የተስፋን ቃል የተቀበለው እርሱም አንድ ልጁን ሊሠዋ ዝግጁ ነበር፤


በላይዋም ማስተስሪያውን የሚጋርዱ የክብር ኪሩቤል ነበር፤ ስለ እነዚህም በዝርዝር የመናገሪያው ሰዓት አሁን አይደለም።


“ኀጢአተኞችን ለማዳን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ፤” የሚለው ቃል የታመነና ሰው ሁሉ ሊቀበለው የሚገባ ነው፤ ከኀጢአተኞችም ዋነኛው እኔ ነኝ፤


ይህም ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን አሁን ዕርቅን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ እንመካለን።


ራሱም ጻድቅ እንዲሆን በኢየሱስም የሚያምነውን እንዲያጸድቅ አሁን በዚህ ዘመን ጽድቁን እንዲያሳይ ነው።


ወይስ የቸርነቱን፥ የቻይነቱን፥ የታጋሽነቱንም ባለጠግነት ትንቃለህን? የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሓ ሊመራህ እንደሆነ አታውቅምን?


እግዚአብሔር ግን ክርስቶስ መከራ እንዲቀበል አስቀድሞም በነቢያት ሁሉ አፍ የተናገረውን እንዲሁ ፈጸመው።


ከጥንት ጀምሮ ሥራቸው ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ነው።’


እርሱንም በእግዚአብሔር በተወሰነው አሳቡና በቀደመው እውቀቱ ተሰጥቶ በዐመፀኞች እጅ ሰቅላችሁ ገደላችሁት።


እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ በእኔ የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው።


ከነፍሱ ሥቃይ ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ አገልጋዬ በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፤ ኃጢአታቸውንም ይሸከማል።


ሰማያት የእርሱን ጽድቅ አወሩ፥ አሕዛብም ሁሉ ክብሩን አዩ።


ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ፥ እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና።


በታላቅ ጉባኤ ጽድቅን አበሠርሁ፥ እነሆ፥ ከንፈሮቼን አላግድም፥ አቤቱ፥ አንተ ታውቃለህ።


ለዐዛዜል ይሆን ዘንድ ዕጣው የወደቀበትን ፍየል እንዲያስተሰርይበት፥ ወደ ምድረ በዳ እንዲሄድ ለመልቀቅ በሕይወቱ እንዳለ በእግዚአብሔር ፊት ያቆመዋል።


ጌታ ማዳኑን አስታወቀ፥ በአሕዛብም ፊት ጽድቁን ገለጠ።


እርሱ ባለፉት ትውልዶች አሕዛብን ሁሉ በገዛ ራሳቸው ጐዳና ይሄዱ ዘንድ ተዋቸው።


እንግዲህ በአንድ ሰው በደል ምክንያት ኩነኔ ለሰው ሁሉ እንደመጣ፥ እንዲሁም በአንድ ሰው የጽድቅ ሥራ ምክንያት ሕይወትን ለማጽደቅ መጣ።


እንግዲህ እርሾ እንደሌለበት እንደ አዲስ ሊጥ እንድትሆኑ፥ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤


እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን ስለ እኛ ኃጢአት የሌለበትን እርሱን ኃጢአት አደረገው።


በእርሱም እንደ ጸጋው ባለጠግነት መጠን፥ በደሙ ቤዛነታችንን አገኘን፤ የበደላችንም ይቅርታ ሆነ።


አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።


እንዲሁም ክርስቶስ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ተሰውቷል። ለሁለተኛ ጊዜ ሲታይ ሊያድናቸው ለሚጠባበቁት ኃጢአትን ለመሸከም ሳይሆን መዳንን ለማምጣት ነው።


እንዲሁም ከታመነው ምስክር፥ ከሙታን በኩር ከሆነው፥ የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ፤ ለወደደን፥ ከኀጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች