Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ራእይ 3:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 “በሎዲቅያም ወዳለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፥ አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ የእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “በሎዶቅያ ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ አሜን የሆነው፣ ደግሞም ታማኝና እውነተኛ ምስክር የሆነው፣ የእግዚአብሔርም ፍጥረት ምንጭ የሆነው እንዲህ ይላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 “ለሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ “ይህ፥ አሜን ከሆነው፥ ታማኝና እውነተኛ ምስክር ከሆነው፥ የእግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ መገኛ ከሆነው የተነገረ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 “በሎዲቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ራእይ 3:14
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርሱም ለማይታየው አምላክ ምሳሌ ነው፤ የፍጥረት ሁሉ በኩር ነው፤


እንዲሁም ከታመነው ምስክር፥ ከሙታን በኩር ከሆነው፥ የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ፤ ለወደደን፥ ከኀጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥


እርሱም አካሉ የሆነችው የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፤ እርሱ በሁሉ ነገር ቀዳሚ በመሆን መጀመሪያ ነው፤ ከሙታንም በኩር ነው።


እግዚአብሔር ለሰጠው የተስፋ ቃል ሁሉ “አዎን” ማለት የእርሱ ነው፤ ስለዚህ ስለ እግዚአብሔር ክብር በእኛ ስለሚነገረው “አሜን” የምንለው እርሱ በኩል ነው።


“በፊላደልፊያም ወዳለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፥ ‘ቅዱስና እውነተኛ የሆነው፥ የዳዊትም መክፈቻ ያለው፥ ሲከፍትም፥ ማንም የማይዘጋው፤ ሲዘጋም ማንም የማይከፍተው፤ እርሱ እንዲህ ይላል’፦


አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።”


ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም ነጭ ፈረስ፤ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፤ በጽድቅም ይፈርዳል፤ ይዋጋልም።


እነርሱም ኤርምያስን እንዲህ አሉት፦ “ጌታ አምላክህ በአንተ አማካይነት ወደ እኛ የላከውን ቃል ሁሉ ባናደርግ፥ ጌታ በመካከላችን እውነተኛና ታማኝ ምስክር ይሁንብን።


እንዲሁም በምድር ላይ የተባረከ በእውነት አምላክ ይባረካል፥ በምድርም ላይ የማለ በእውነት አምላክ ይምላል፤ ምክንያቱም የቀድሞው ጭንቀት ተረስቶአል፥ ከዓይኔም ተሰውሮአል።


ጌታ የመንገዱ መጀመሪያ አደረገኝ፥ በቀድሞ ሥራው መጀመሪያ።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸው፤ የነቢያትም መናፍስት ጌታ አምላክ በቶሎ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለባርያዎቹ እንዲያሳይ መልአኩን ሰደደ።”


እንዲህም አለኝ፦ “ተፈጽሞአል፤ አልፋና ዖሜጋ፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ። ለተጠማ ከሕይወት ውሃ ምንጭ በነጻ እኔ እሰጣለሁ።


እንዲሁም “የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ማለትም ወደ ኤፌሶንና ወደ ሰምርኔስ ወደ ጴርጋሞንም ወደ ትያጥሮንም ወደ ሰርዴስም ወደ ፊላደልፊያም ወደ ሎዲቅያም ላክ፤ አለኝ።”


“በኤፌሶን ወዳለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፥ በቀኝ እጁ ሰባቱን ከዋክብት የያዘው በሰባቱም የወርቅ መቅረዞች መካከል የሚመላለሰው እንዲህ ይላል፦


ይህም መልእክት በእናንተ ዘንድ ከተነበበ በኋላ፥ በሎዶቅያ ሰዎች ማኅበር ደግሞ እንዲነበብ አድርጉ፤ ከሎዶቅያም የምታገኙትን መልእክት እናንተ ደግሞ አንብቡ።


ስለ እናንተና በሎዶቅያ ስላሉት ፊቴንም አይተውት ስለማያውቁት ሰዎች ሁሉ ምን ያኽል እንደምጋደል እንድታውቁ እወዳለሁና፤


እነሆ፥ ለአሕዛብ ምስክር፥ ለወገኖችም አለቃና አዛዥ እንዲሆን ሰጥቼዋለሁ።


ሮቤል፥ አንተ በኩር ልጄና ኃይሌ፥ የጉብዝናዬም መጀመሪያ፥ የክብር አለቃና የኃይል አለቃ።


ይልቁንም ከተጠላችው ሚስቱ ለተወለደው ልጅ ካለው ሀብት ሁሉ ሁለት እጅ ድርሻውን በመስጠት ብኩርናውን ያስታውቅ፤ ያ ልጅ የአባቱ ኃይል መጀመሪያ ነውና፤ የብኩርና መብት የእርሱ ነው።


የታመነ ምስክር አይዋሽም፥ የሐሰት ምስክር ግን በሐሰት ይናገራል።


ሁሉ በእርሱ ሆነ፤ ከሆነውም ሁሉ አንድም ነገር ያለ እርሱ የሆነ የለም።


ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔ ስለ እራሴ ምንም እንኳ ብመሰክር ከወዴት እንደመጣሁ ወዴትም እንድምሄድ አውቃለሁና ምስክርነቴ እውነት ነው፤ እናንተ ግን ከወዴት እንደመጣሁ ወዴትም እንደምሄድ አታውቁም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች