Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ራእይ 15:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በእሳትም የተቀላቀለውን የብርጭቆ ባሕር የሚመስለውን አየሁ፤ በአውሬውና በምስሉም በስሙም ቍጥር ላይ ድል ነሥተው የነበሩት የእግዚአብሔርን በገና ይዘው በብርጭቆ ባሕር ላይ ሲቆሙ አየሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ከእሳት ጋራ የተቀላቀለ የብርጭቆ ባሕር የሚመስል አየሁ፤ በባሕሩም አጠገብ አውሬውን፣ ምስሉንና የስሙን ቍጥር ድል የነሡትን ቆመው አየሁ፤ እነርሱም ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን በገና ይዘው፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ከዚህ በኋላ እሳት የተቀላቀለበት የመስተዋት ባሕር የሚመስል ነገር አየሁ፤ እንዲሁም አውሬውንና የአውሬውን ምስል፥ የስሙንም ቊጥር ምልክት ድል የነሡትን አየሁ፤ እግዚአብሔር የሰጣቸውን በገና ይዘው በመስተዋቱ ባሕር አጠገብ ቁመው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በእሳትም የተቀላቀለውን የብርጭቆ ባሕር የሚመስለውን አየሁ፤ በአውሬውና በምስሉም በስሙም ቍጥር ላይ ድል ነሥተው የነበሩት የእግዚአብሔርን በገና ይዘው በብርጭቆ ባሕር ላይ ሲቆሙ አየሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በእሳትም የተቀላቀለውን የብርጭቆ ባሕር የሚመስለውን አየሁ፥ በአውሬውና በምስሉም በስሙም ቍጥር ላይ ድል ነሥተው የነበሩት የእግዚአብሔርን በገና ይዘው በብርጭቆ ባሕር ላይ ሲቆሙ አየሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ራእይ 15:2
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዐይኖች የሞሉአቸው አራት ሕያዋን ፍጡራን ነበሩ።


እነርሱም በበጉ ደምና በምስክራነታቸው ቃል ድል ነሡት፤ ሞትን እስኪሸሹ ድረስ ነፍሳቸውንም አልወደዱም።


መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ ሕያዋን ፍጡራን ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፤ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ሳሕን ያዙ።


ቅጥርዋም ከኢያሰጲድ የተሠራ ነበረ፤ ከተማይቱም የጠራ ብርጭቆ የሚመስል ንጹሕ ወርቅ ነበረች።


በዚህም በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ ነው።


“እኔ ለንስሐ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን ለመሸከም የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፤


በአውሬውም ፊት እንዲያደርግ ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታል፤ የሰይፍም ቁስል ለነበረውና በሕይወት ለኖረው ለአውሬው ምስልን እንዲሠሩ በምድር የሚኖሩትን ያዛቸዋል።


ወዳጆች ሆይ! እንደ እሳት በሚፈትን መከራ ውስጥ ስትገኙ ያልተለመደ እንግዳ ነገር እንደ ደረሰባችሁ አድርጋችሁ አትደነቁ።


ከዚያም አንድ አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ ዐሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፤ በቀንዶቹም ላይ ዐሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።


የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሰው ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችልም ያደርጋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች