Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ራእይ 14:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ከሰማይም እንደ ብዙ ውሃ ድምፅና እንደ ታላቅ ነጐድጓድ ድምፅ የመሰለ ድምፅን ሰማሁ፤ የሰማሁትም ድምፅ ደርዳሪዎች በበገናቸው ሲደረድሩ እንደሚሰማው ዓይነት ድምፅ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ከሰማይ እንደ ብዙ ውሃ ድምፅና እንደ ታላቅ ነጐድጓድ ድምፅ የመሰለ ድምፅ ሰማሁ፤ የሰማሁት ድምፅ በገና ደርዳሪዎች እንደሚደረድሩት ዐይነት ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ከሰማይም የታላቅ ፏፏቴ ውሃ ድምፅና ታላቅ ነጐድጓድ የመሰለ ከፍተኛ ድምፅ ሰማሁ፤ የሰማሁትም ድምፅ በገና ደርዳሪዎች በገና እየደረደሩ የሚያሰሙትን ድምፅ ይመስል ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እንደ ብዙ ውሃም ድምፅና እንደ ታላቅ ነጐድጓድ ድምፅ ያለ ከሰማይ ድምፅን ሰማሁ፤ ደርዳሪዎችም በገና እንደሚደረድሩ ያለ ድምፅ ሰማሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እንደ ብዙ ውኃም ድምፅና እንደ ታላቅ ነጐድጓድ ድምፅ ያለ ከሰማይ ድምፅን ሰማሁ፥ ደርዳሪዎችም በገና እንደሚደረድሩ ያለ ድምፅ ሰማሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ራእይ 14:2
29 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ ሕያዋን ፍጡራን ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፤ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ሳሕን ያዙ።


እግሮቹም በምድጃ ውስጥ የነጠረ የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፤ ድምፁም እንደ ብዙ ውሃዎች ድምፅ ነበረ።


በእሳትም የተቀላቀለውን የብርጭቆ ባሕር የሚመስለውን አየሁ፤ በአውሬውና በምስሉም በስሙም ቍጥር ላይ ድል ነሥተው የነበሩት የእግዚአብሔርን በገና ይዘው በብርጭቆ ባሕር ላይ ሲቆሙ አየሁ።


ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም እንዲህ የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ፦ “የዓለም መንግሥት የጌታችንና የመሢሑ ሆነች፤ ለዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል፤”


እነሆ፥ የእስራኤል አምላክ ክብር ከወደ ምሥራቅ መጣ፤ ድምፁም እንደ ብዙ ውኆች ድምጽ ነበር፥ ከክብሩ የተነሣ ምድር ታበራ ነበር።


ጌታን በመሰንቆ አመስግኑት፥ ዐሥር አውታርም ባለው በገና ዘምሩለት።


ዳዊትና የእስራኤል ቤት በሙሉ በዝማሬ፥ በበገና፥ በመሰንቆ፥ በከበሮ፥ በጽናጽልና በቃጭል ድምፅ በጌታ ፊት ያሸበሽቡ ነበር።


እንዲህም ሆነ በሦስተኛው ቀን ማለዳ ነጎድጓድ፥ መብረቅና ከባድ ደመና እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምጽ በተራራው ላይ ሆነ፤ በሰፈሩ የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ።


ከእንግዲህ ወዲህ በገና የሚመቱና የሚዘምሩ ሰዎች ድምፅ፥ እንቢልታንና መለከትንም የሚነፉ ሰዎች ድምፅ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ የማንኛውም ዕደ ጥበብ ብልሃተኛ ሰው ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይገኝም፤ የወፍጮ ድምጽም ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤


በሰማይም “ወደዚህ ውጡ” የሚላቸውን ታላቅ ድምፅ ሰሙ፤ ጠላቶቻቸውም እየተመለከቱአቸው ወደ ሰማይ በደመና ወጡ።


በጉም ከሰባቱ ማኅተሞች አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፤ ከአራቱም ሕያዋን ፍጡራን አንዱ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ “ና” ሲል ሰማሁ።


በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፤ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ፤


ከብዙ ውኆች ድምፅ ከባሕርም ታላቅ ሞገድ ይልቅ ጌታ በከፍታው ድንቅ ነው።


በማለዳ ምሕረትን፥ በሌሊትም እውነትህን ማውራት


ልቤ ጽኑ ነው፥ አቤቱ፥ ልቤ ጽኑ ነው፥ እቀኛለሁ፥ እዘምራለሁ።


የፊተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ደምም የተቀላቀለበት በረዶና እሳት ሆነ፤ ወደ ምድርም ተጣለ፤ የምድርም ሲሶው ተቃጠለ፤ የዛፎችም ሲሶው ተቃጠለ፤ የለመለመም ሣር ሁሉ ተቃጠለ።


ጌታም በእነርሱ ላይ ይገለጣል፥ የአምላኩም ቀስት እንደ መብረቅ ይወጣል፤ እግዚአብሔር ጌታም መለከትን ይነፋል፥ ከደቡብም ዐውሎ ነፋስ ይመጣል።


ሕዝቦች እንደ ብዙ ውኃ ጩኸት ይጮኻሉ፤ እርሱ ግን ይገሥጻቸዋል፤ እነርሱም እየሸሹ ይርቃሉ፤ በተራራም ላይ እንዳለ እብቅ በነፋስ ፊት፥ ዐውሎ ነፋስ እንደሚያዞረውም ትቢያ ይበተናሉ።


ስሙን በሽብሸባ ያወድሱ፥ በከበሮና በመሰንቆም ይዘምሩለት።


ለጌታ በመሰንቆ፥ በመሰንቆና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩ።


ሕዝቡም ሁሉ ነጎድጓዱንና መብረቁን፥ የቀንደ መለከቱን ድምፅ፥ ተራራውንም ሲጤስ አዩ፤ ሕዝቡም ፈሩ ተንቀጠቀጡም፥ ርቀውም ቆሙ።


ለጌታ በምስጋና ዘምሩ፥ ለአምላካችንም በመሰንቆ ዘምሩ፥


ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ፥ ጉልማስነቴንም ደስ ወዳሰኛት ወደ አምላኬ እገባለሁ፥ አቤቱ አምላኬ፥ በበገና አመሰግንሃለሁ።


በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር፥ ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሿሿ ጸናጽል ነኝ።


በበገናና በመሰንቆ በመለከትም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ጌታ ቤት ገቡ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች