Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ራእይ 14:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ሌላም መልአክ ከመቅደሱ ወጥቶ በደመናው ላይ ለተቀመጠው “የማጨድ ሰዓት ስለ ደረሰ ማጭድህን ስደድና እጨድ፤ የምድሪቱ መከር ደርሶአልና፤” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሌላም መልአክ ከመቅደሱ ወጥቶ በደመናው ላይ ለተቀመጠው፣ “የዐጨዳው ሰዓት ስለ ደረሰ፣ ማጭድህን ይዘህ ዕጨድ፤ የምድር መከር ደርሷልና” ሲል በታላቅ ድምፅ ጮኸ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ሌላ መልአክ ከመቅደሱ ወጣና በደመና ላይ የተቀመጠውን ከፍ ባለ ድምፅ “የምድር መከር ደርሶአል! የዐጨዳ ሰዓትም ቀርቦአል!”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ሌላ መልአክም ከመቅደሱ ወጥቶ በደመናው ላይ ለተቀመጠው “የማጨድ ሰዓት ስለ ደረሰ ማጭድህን ስደድና እጨድ፤ የምድሪቱ መከር ጠውልጓልና፤” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ሌላ መልአክም ከመቅደሱ ወጥቶ በደመናው ላይ ለተቀመጠው፦ የማጨድ ሰዓት ስለ ደረሰ ማጭድህን ስደድና እጨድ፥ የምድሪቱ መከር ጠውልጓልና ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ራእይ 14:15
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መከሩ ደርሶአልና ማጭድ ስደዱ፥ መጥመቂያውም ሞልቶአልና ኑ እርገጡ፥ ክፉታቸውም በዝቶአልና መጥመቂያ ሁሉ ፈርሶአል።


ፍሬ ግን ሲበስል መከር ደርሷአልና ወዲያው ማጨድ ይጀምራል።”


የዘራው ጠላት ደግሞ ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፤ አጫጆቹ መላእክት ናቸው።


የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ “የባቢሎን ሴት ልጅ በመረገጥ ላይ እንዳለ ዐውድማ ነች፤ ጥቂት ቈይታ የመከር ጊዜ ይደርስባታል።”


በእሳትም ላይ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከመሠዊያው ወጥቶ ስለታም ማጭድ ያለውን “ዘለላዎቹ በስለዋልና ስለታሙን ማጭድህን ስደድና በምድር ያለውን የወይን ዛፍ ዘለላዎች ቁረጥ፤” ብሎ በታላቅ ድምፅ ተጣራ።


እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ ተዉአቸው፤ በመከር ጊዜ አጫጆቹን “አስቀድማችሁ እንክርዳዱን በእሳትም ለማቃጠል ሰብስባችሁ በየነዶው እሰሩት፤ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱት፤ እላቸዋለሁ።”


ሰባተኛውም መልአክ ጽዋውን በአየር ላይ አፈሰሰ፤ ከመቅደሱም ውስጥ “ተፈጸመ!” የሚል ታላቅ ድምጽ ከዙፋኑ ወጣ።


እናንተ ደግሞ የአባቶቻችሁን መስፈሪያ ፈጽሙ።


ሰባቱንም መቅሠፍት የያዙ ሰባቱ መላእክት ከመቅደሱ ወጡ፤ ከተልባ እግርም የተሠራ ንጹሕ የጌጥ ልብስ ለበሱ፤ ደረታቸውንም በወርቅ መታጠቂያ ታጠቁ።


ከዚያም አየሁ፤ እነሆም ነጭ ደመና በደመናውም ላይ የሰው ልጅን የሚመስል ተቀምጦአል፤ በራሱም ላይ የወርቅ አክሊል በእጁም ስለታም ማጭድ ነበረው።


በታላቅ ድምፅም እየጮኹ “ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ! እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?” አሉ።


ለአሕዛብ እንዳንናገር በመከልከል እነርሱ እንዳይድኑ ያደርጋሉ፤ በዚህም ያለማቋረጥ የኃጢአታቸውን መስፈርያ ይሞላሉ፤ ነገር ግን በመጨረሻ የእግዚአብሔር ቁጣው ይመጣባቸዋል።


በመጀመሪያው አውሬ ስም፥ በሙሉ ሥልጣን ይሠራ ነበር። ወደ ሞት የሚያደርሰው ቁስል ለተፈወሰለትም ለፊተኛው አውሬ ምድርና በእርሱ የሚኖሩት እንዲሰግዱለት ያደርጋል።


ጽድቅዋ እንደ ጸዳል መዳንዋም እንደሚበራ ፋና እስኪ ወጣ ድረስ፥ ስለ ጽዮን ዝም አልልም፥ ስለ ኢየሩሳሌምም አላርፍም።


አብራምም በእግዚአብሔር አመነ፥ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት።


በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተከፈተ፤ የኪዳኑም ታቦት በቤተ በመቅደሱ ታየ፤ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።


በደመናውም ላይ የተቀመጠው ማጭዱን ወደ ምድር ጣለው፤ ምድርም ታጨደች።


ሌላም መልአክ በሰማይ ካለው መቅደስ ወጣ፤ እርሱም ደግሞ ስለታም ማጭድ ነበረው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች