Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ራእይ 13:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እሳትንም እንኳ ከሰማይ ወደ ምድር በሰዎች ፊት እስኪያወርድ ድረስ ታላላቅ ምልክቶችን ያደርጋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በሰዎቹም ፊት እሳት ከሰማይ ወደ ምድር እስኪያወርድ ድረስ ታላላቅ ምልክቶችን አደረገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ይህ ሁለተኛው አውሬ ግን በሰዎች ፊት እሳትን ከሰማይ እስከማውረድ ድረስ ታላላቅ ተአምራትን ያደርግ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እሳትንም እንኳ ከሰማይ ወደ ምድር በሰው ፊት እስኪያወርድ ድረስ ታላላቆችን ምልክቶች ያደርጋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እሳትንም እንኳ ከሰማይ ወደ ምድር በሰው ፊት እስኪያወርድ ድረስ ታላላቆችን ምልክቶች ያደርጋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ራእይ 13:13
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚህ በኋላ ጌታ እሳትን ላከ፤ ያም እሳት መሥዋዕቱን፥ እንጨቱንና ድንጋዩን አቃጠለ፤ ምድሩንም ለበለበ፤ በጉድጓዱ የነበረውንም ውሃ አደረቀ፤


የግብጽም አስማተኞች በአስማታቸው እንዲሁ አደረጉ፤ የፈርዖንም ልብ ጸና፥ ጌታም እንደ ተናገረ አልሰማቸውም።


እንቁራሪቶቹን ከአንተ ከቤቶችህም ከአገልጋዮችህም ከሕዝብህም ያርቃል፤ በዓባይ ወንዝ ብቻ ይቀራሉ።”


ብጉንጅ በጠንቋዮቹና በግብጻውያን ሁሉ ላይ ነበር፤ ጠንቋዮቹም ብጉንጅ ስለ ነበረባቸው በሙሴ ፊት መቆም አልቻሉም፤


እሳትም ከጌታ ዘንድ ወጥቶ ያጥኑ የነበሩትን ሁለት መቶ ኀምሳ ሰዎች በላቸው።


ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ሊፈትኑት መጡና ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ጠየቁት።


ሐሰተኞች መሲሖችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፤ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ ለማሳት ታላላቅ ምልክትንና ድንቅ ነገሮችን ያሳያሉ።


ሐሰተኛ ክርስቶሶችና ሐሰተኛ ነቢያት ተነሥተው፥ ምልክቶችንና ድንቆችን በማድረግ፥ ቢቻላቸው የተመረጡትን እንኳ ያስታሉ።


ኢያኔስና ኢያንበሬስም ሙሴን እንደ ተቃወሙት፥ እንዲሁ እነዚህ ደግሞ አእምሮአቸው የጠፋባቸው በእምነትም ረገድ ተፈትነው የወደቁ ሰዎች ሆነው እውነትን ይቃወማሉ።


ማንም ሊጐዳቸው ቢወድ እሳት ከአፋቸው ይወጣል፤ ጠላቶቻቸውንም ይበላል፤ ማንም ሊጐዳቸው ቢወድም እንዲሁ ሊገደል ይገባዋል።


የአጋንንት መናፍስት ናቸውና፥ ምልክት እያደረጉ፥ በታላቁና ሁሉን በሚገዛው በእግዚአብሔር ቀን ለሚሆነው ጦርነት እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ።


አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛውም ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።


ወደ ምድርም ስፋት ወጡ፤ የቅዱሳንንም ሰፈርና የተወደደችውን ከተማ ከበቡ፤ ነገር ግን እሳት ከሰማይ ወርዳ በላቻቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች