Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 95:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እርሱ አምላካችን ነውና፥ እኛ የማሰማርያው ሕዝብ የእጁም በጎች ነንና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እርሱ አምላካችን ነውና፤ እኛም በእጁ ጥበቃ ሥር ያለን በጎቹ፣ የመሰማሪያውም ሕዝብ ነን። ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እርሱ አምላካችን ነው፤ እኛም እርሱ የሚጠነቀቅልን ሕዝቦቹና የሚያሰማራን መንጋዎቹ ነን፤ ስለዚህ ዛሬ እንዲህ ሲል የሚናገረውን አድምጡ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የአ​ሕ​ዛብ ወገ​ኖች፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ፥ ክብ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 95:7
28 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርሱ ጌታ አምላካችን ነው፤ ፍርዱ በምድር ሁሉ ነው።


ጌታ እርሱ አምላክ እንደሆነ እወቁ፥ እርሱ ሠራን፥ እኛም የእርሱ ነን፥ እኛስ ሕዝቡ የማሰማርያውም በጎች ነን።


አምላካችንስ በላይ በሰማይ ነው፥ የፈቀደውን ሁሉ አደረገ።


የዳዊት መዝሙር። ጌታ እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።


በብርታትዋ ልባችሁን አኑሩ፥ ቅጥሮችዋን መርምሩ፥ ለሚመጣው ትውልድ ትነግሩ ዘንድ።


አቤቱ፥ አሕዛብ ያመስግኑህ፥ አሕዛብ ሁሉ ያመስግኑህ።


የአሳፍ ትምህርት። አቤቱ፥ ስለምን ለሁልጊዜ ጣልኸኝ? በማሰማርያህ በጎች ላይስ ቁጣህ ስለምን ጨሰ?


እኛ ሕዝብህ ግን፥ የማሰማርያህም በጎች፥ ለዘለዓለም እናመሰግንሃለን፥ ለልጅ ልጅም ምስጋናህን እንናገራለን።


ጌታ ኃይሌና መዝሙሬ ነው፥ መድኃኒቴም ሆነልኝ፤ ይህ አምላኬ ነው አመሰግነዋለሁም፥ የአባቴ አምላክ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።


“ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ ጌታ አምላክህ እኔ ነኝ።


ክቡር ነገርን እናገራለሁና ስሙ፥ ከንፈሮቼም ቅን ነገርን ለመናገር ይከፈታሉ።


ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ፤ ሰውነታችሁ በሕይወት እንድትኖር ስሙኝ፥ የታመነችይቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘለዓለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።


ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የማደርገው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።


በአትክልት ቦታ መካከል ባለው ጥሻ ብቻቸውን የተቀመጡት የርስትህን መንጋ፥ ሕዝብህን በበትርህ ጠብቅ፤ እንደ ቀደመው ዘመን በበሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።


እርሱም ገና እየተናገረ ሳለ እነሆ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆ ከደመናው ውስጥ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የተወደደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ መጣ።


በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።


አሁን ግን የሚበልጠውን ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ። ስለዚህ እግዚአብሔር ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና አምላካቸው ተብሎ ለመጠራት በእነርሱ አያፍርም።


ነገር ግን ከእናንተ በኃጢአት ተታሎ ልቡን እምቢተኛ እንዳያደርግ፥ “ዛሬ” ተብሎ የተጠራው ጊዜ እስካለ ድረስ፥ በየቀኑ እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ።


“ዛሬ ድምጹን ብትሰሙት፥ በማስመረር እንደሆነ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ፤” እንደተባለው ነው።


ይህም አስቀድሞ እንደተባለው፥ “ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ፤” በፊት እንደተባለ፥ ይህን ከሚያህል ዘመን በኋላ በዳዊት ሲናገር “ዛሬ” ብሎ አንድ ቀን እንደገና ይቀጥራል።


እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበር፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።


እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ፤ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ፤ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች