Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 91:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ከሌሊት ሽብር፥ በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የሌሊትን አስደንጋጭነት፣ በቀን የሚወረወረውንም ፍላጻ አትፈራም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “በሌሊት ሽብር ይደርስብኛል፤ በቀን ፍላጻ ይወረወርብኛል” ብለህ አትፈራም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 አቤቱ፥ ሥራህ እጅግ ትልቅ ነው፥ አሳ​ብ​ህም እጅግ ጥልቅ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 91:5
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህም የሆነበት ምክንያት እግዚአብሔር ሶርያውያንን በፈረሶችና በሠረገሎች የታጀበ የብዙ ሠራዊት ግሥጋሤ የሚመስል ድምፅ አሰምቶአቸው ስለ ነበር ነው፤ ይኸውም ሶርያውያን እንዳሰቡት የእስራኤል ንጉሥ የሒታውያንና የግብጽ ነገሥታትን ከነሠራዊቶቻቸው ቀጥሮ አደጋ ሊጥልባቸው የመጣ መስሎአቸው ነበር።


ሁሉን የሚችል የአምላክ ፍላጻ በሥጋዬ ውስጥ ነው፥ መርዙንም ነፍሴ ትጠጣለች፥ የእግዚአብሔር ሽብሮች በኔ ላይ ተሰልፈዋል።


ክፉ ዜናን አይፈራም፥ ልቡ የጸና፥ በጌታም የታመነ ነው።


አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው።


ክፉ ማንም ሳያሳድደው ይሸሻል፥ ጻድቅ ግን እንደ አንበሳ ተማምኖ ይኖራል።


ሁሉም ሰይፍ የያዙና ጦርነት የለመዱ ናቸው፥ በሌሊት ከሚከሰት አደጋ የተነሣ ሰው ሁሉ ሰይፉ በወገቡ አለ።


ልቤ ራደ፥ ድንጋጤ አስደመመኝ፥ ተስፋ ያደረግሁትም ድንግዝግዝታ ፍርሃት አሳደረብኝ።


በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰምጡህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም።


እርሱም “እናንተ እምነት የጎደላችሁ! ለምን ትፈራላችሁ?” አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸው፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።


እግዚአብሔር ግን ‘አንተ ሰነፍ! በዚች ሌሊት ነፍስህን ከአንተ ሊወስዱአት ይፈልጓታል፤ ይህስ የሰበሰብኸው ለማን ይሆናል?’ አለው።


ይህን ግን እወቁ ባለቤት በምን ሰዓት ሌባ እንደሚመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ፥ ቤቱም እንዲቆፈር ባልፈቀደም ነበር።


ስለዚህ በመተማመን፥ “ጌታ ይረዳኛልና አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል?” እንላለን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች