Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 90:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት፥ ቢበረታም ሰማንያ ዓመት ነው፥ ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው፥ ከእኛ ቶሎ ያልፋልና፥ እኛም እንጠፋለንና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የዕድሜያችን ዘመን ሰባ ዓመት፣ ቢበዛም ሰማንያ ነው፤ ከዚያ በላይ ከሆነም ድካምና መከራ ብቻ ነው፤ ቶሎ ያልፋልና፤ እኛም ወዲያው እንነጕዳለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ዕድሜአችን ሰባ ዓመት ነው፤ ቢበዛም ሰማኒያ ዓመት ነው፤ እነዚያም ዘመናት በችግርና በሐዘን የተሞሉ ናቸው፤ ዕድሜአችን በቶሎ ያልቃል፤ እኛም እናልፋለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ክፉ ነገር ወደ አንተ አይ​ቀ​ር​ብም፥ መቅ​ሠ​ፍ​ትም ወደ ቤትህ አይ​ገ​ባም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 90:10
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገ የሚሆነውን አታውቁም። ሕይወታችሁ ምንድነው? ለጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፋሎት አይደላችሁምን?


ወጥቶ የማይመለስ ነፋስ፥ ሥጋም እንደ ሆኑ አሰበ።


ባርዚላይ ግን ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ከንጉሡ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም የምሄደው ለየትኛው ዕድሜዬ ብዬ ነው?


ያዕቆብም ለፈርዖን አለው፦ “የእንግድነቴ ዘመን መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፥ የሕይወቴ ዘመኖች ጥቂትም ክፋም ሆኑብኝ፥ አባቶቼ በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም።”


ሙሴም በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሀያ ዓመት ነበረ፥ ዓይኑ አልፈዘዘም፥ ጉልበቱም አልደነገዘም።


ንጉሡ ዳዊትም ዕድሜው ገፍቶ ስለ ሸመገለ፥ ልብስ ደራርበው ቢያለብሱትም ሙቀት ሊሰጠው አልቻለም ነበር።


ጥቂት ጊዜ ከፍ ከፍ ይላሉ፥ ይሄዳሉ፥ ይጠወልጋሉም፥ እንደ ሌሎች ሁሉ ይከማቻሉ፥ እንደ እሸትም ራስ ይቈረጣሉ።


ሰው ግን ይሞትና ይጋደማል፥ ሰውም ነፍሱ ትወጣለች፥ እርሱስ ወዴት አለ?


ማደሪያዬ ተነቀለች፥ እንደ እረኛ ድንኳንም ከእኔ ዘንድ ተወገደች፤ ሕይወቴንም እንደ ሸማኔ ጠቀለልኩት፤ እርሱም ከመጠቅለያው ይቈርጠኛል፤ ከጠዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ፍጻሜዬን አቀረብከው።


እግዚአብሔር ግን ‘አንተ ሰነፍ! በዚች ሌሊት ነፍስህን ከአንተ ሊወስዱአት ይፈልጓታል፤ ይህስ የሰበሰብኸው ለማን ይሆናል?’ አለው።


እንደ ሕልም ይበርራል፥ እርሱም አይገኝም፥ እንደ ሌሊትም ራእይ ይሰደዳል።


ጌታም፦ “መንፈሴ በሰው ላይ ለዘለዓለም አይኖርም፥ እርሱ ሥጋ ነውና፥ እድሜውም መቶ ሃያ ዓመት ይሆናል” አለ።


ዕድሜውም ስልሳ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆነው ሰው ቢሆን ለወንድ ግምትህ ዐሥራ አምስት ሰቅል፥ ለሴትም ዐሥር ሰቅል ይሁን።


ሙሴም በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርሁ እንዲሁ ዛሬም ብርቱ ነኝ፤ ጉልበቴም በዚያን ጊዜ እንደ ነበረ፥ እንዲሁ ዛሬ ለመዋጋት ለመውጣትም ለመግባትም ጉልበቴ ያው ነው።


እኔ አሁን የሰማንያ ዓመት ሽማግሌ ነኝ፤ ታዲያ የሚያስደስቱና የማያስደስቱ ነገሮችን መለየት እችላለሁን? ከእንግዲህ አገልጋይህ የሚበላውንና የሚጠጣውን ጣዕሙን መለየት ይችላል? የሚዘፍኑትን የወንዶችና የሴቶችን ድምፅ አሁንስ መስማት እችላለሁ? ታዲያ አገልጋይህ ለንጉሥ ጌታዬ ለምን ተጨማሪ ሸክም ይሆናል?


ሰው ለመከራ ተወልዶአል የአሞራ ግልገሎች ወደ ላይ እየበረሩ ከፍ እንደሚሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች