Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 9:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ድሀ ለዘለዓለም አይረሳምና፥ የችግረኞችም ተስፋቸው ለዘለዓለም አይጠፋም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ፤ ሰውም አያይል፤ አሕዛብም በፊትህ ይፈረድባቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 አምላክ ሆይ! ሰዎች በብርታታቸው እንዳይጓደዱብህ ተነሥ፤ በአሕዛብም ላይ ፍረድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 አቤቱ፥ ተነሥ፥ ሰውም አይ​በ​ርታ፥ አሕ​ዛ​ብም በፊ​ትህ ይፈ​ረ​ድ​ባ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 9:19
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሚከቡኝን አእላፍ ሕዝብ አልፈራም።


ነፍሳችን በመሬት ላይ ተጐሳቁላለችና፥ ሆዳችንም ከምድር ጋር ተጣብቃለችና።


ስለ አንተ ሁልጊዜ ተገድለናል፥ እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል።


አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ተነሥ እጅህንም ከፍ ከፍ አድርግ፥ ድሆችን አትርሳ።


ጠላት ነፍሴን ያሳድዳት ያግኛትም፥ ሕይወቴንም በምድር ላይ ይርገጣት፥ ክብሬንም በትቢያ ላይ ያዋርዳት።


ስለዚህ “ጠብቁኝ” ይላል ጌታ፤ ለመበዝበዝ እስከምነሣበት ቀን ድረስ፥ ፍርዴ ሕዝቦችን ለመሰብሰብ፥ መንግሥታትንም ለማከማቸት ነው፥ ይህም መዓቴንና የቁጣዬን ትኩሳት ሁሉ ለማፍሰስ ነው፤ በቅንዓቴ እሳት ምድርም ሁሉ ትበላለችና።


የጌታ ክንድ ሆይ! ተነሥ፥ ተነሥ፥ ኃይልንም ልበስ፤ በቀድሞው ወራትና በጥንቱ ዘመን በነበረው ትውልድ እንደ ሆነው ተነሥ። ረዓብን የቈራረጥህ ዘንዶውንም የወጋህ አንተ አይደለህምን?


በአሕዛብ ላይ በቀልን፥ በሰዎችም መካከል ቅጣትን ያደርጉ ዘንድ፥


በማያውቁህ አሕዛብ ላይ፥ ስምህንም በማይጠሩ መንግሥታት ላይ መዓትህን አፍስስ፥


አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቁጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል።


የግብጽም ወገን ባይወጣ ወደዚያም ባይሄድ፥ ጌታ የዳስ በዓልን ለማክበር የማይወጡትን አሕዛብ የሚቀሥፍበት ቸነፈር በእርሱ ላይ ይመጣል።


አሕዛብ ይነሡ፥ ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆም ይውጡ፥ በዙሪያ ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ እፈርድ ዘንድ በዚያ እቀመጣለሁና።


ያዕቆብን በልተውታልና፥ ውጠውታልምና፥ አጥፍተውታልምና፥ ማደሪያውንም አፍርሰዋልና በማያውቁህ አሕዛብ ስምህንም በማይጠሩ ወገኖች ላይ መዓትህን አውርድ።


ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ፥ የእስራኤል ጠባቂ ሆይ፥ አድምጥ፥ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ፥ ብርሃንህን አብራ።


አሳም እንዲህ ብሎ ወደ አምላኩ ወደ ጌታ ጮኸ፦ “አቤቱ፥ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አይሳንህምና፤ አቤቱ አምላካችን ሆይ! በአንተ ታምነናልና፥ በስምህም በዚህ ታላቅ ወገን ላይ መጥተናልና እርዳን፤ አቤቱ፥ አምላካችን አንተ ነህ፤ ሰውም አያሸንፍህ።”


እርሱ የታማኞቹን እግር ይጠብቃል ሰው በኃይሉ አይበረታምና፥ ኃጥአን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይጣላሉ።


ሰውየውም፦ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ ያዕቆብ አይባልም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና እስራኤል ይባላል” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች