Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 89:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ዘርህን ለዘለዓለም አዘጋጃለሁ፥ ዙፋንህንም ለልጅ ልጅ እመሠርታለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰማያት ድንቅ ሥራህን፣ ታማኝነትህንም በቅዱሳን ጉባኤ መካከል ያወድሳሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እግዚአብሔር ሆይ! ሰማያት ድንቅ ሥራዎችህን ያመስግኑ የሰማያዊው የቅዱሳን ጉባኤም ታማኝነትህን ከፍ ከፍ ያድርጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ዘመ​ኖች በፊ​ትህ የተ​ናቁ ናቸው፥ በማ​ለ​ዳም እንደ ሣር ያል​ፋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 89:5
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰማያት የእርሱን ጽድቅ አወሩ፥ አሕዛብም ሁሉ ክብሩን አዩ።


ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።


ሰማያት ሆይ፥ ጌታ አድርጎታልና ዘምሩ፤ ጌታ ያዕቆብን ተቤዥቶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ ይከበራልና አንተ የምድር ጥልቅ ሆይ፥ ጩኽ፤ እናንተም ተራሮች አንተም ዱር በአንተም ያለ ዛፍ ሁሉ፥ እልል በሉ።


ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ፥ እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና።


ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን በነገሯችሁ ነገር፥ እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፥ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ።


እንዲሁም እርሱ ጌታ ኢየሱስ ከኃያላን መላእክቱ ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል በሚመጣበት ጊዜ መከራን ለተቀበላችሁት ከእኛ ጋር ዕረፍትን ይሰጣችኋል፤


በዚህም ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት እንድትታወቅ ነው።


ጌታን በደመናት የሚተካከለው ማን ነው? ከአማልክትስ ልጆች ጌታን ማን ይመስለዋል?


“አሁንም ተጣራ፥ የሚመልስልህ አለን? ከቅዱሳንስ ወደማናቸው ትዞራለህ?


እንዲህም አለ፦ “ጌታ ከሲና ተራራ መጣ፥ በሴይርም እንደ ንጋት ተገለጠ፥ ከፋራን ተራራ አበራላቸው፥ በስተቀኙም ከእሳት ነበልባል ጋር፥ ከአእላፋት ቅዱሳኑም ጋር መጣ።


ወደ አባቶችህም ለመሄድ ዕድሜህ በተፈጸመ ጊዜ ከልጆችህ የሚሆነውን ዘርህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ።


እርሱ ቤት ይሠራልኛል፤ ዙፋኑንም ለዘለዓለም አጸናለሁ።


በእግዚአብሔር ፊት ለዘለዓለም ይኖራል፥ ይጠብቁት ዘንድ ቸርነትንና እውነትን አዘጋጅለት።


ዘሩንም ለዓለምና ለዘለዓለም፥ ዙፋኑንም እንደ ሰማይ ዘመን አደርጋለሁ።


ዘሩ ለዘለዓለም፥ ዙፋኑም በፊቴ እንደ ፀሐይ ይኖራል።


ጌታ ለዳዊት በእውነት ማለ አይጸጸትምም፥ እንዲህ ብሎ፦ ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።


ለመንግሥቱ ስፋት፤ ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም፤ መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤ ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል። በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤ አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ የዘለዓለም አባት ቅናት ይህን ያደርጋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች