40 የአገልጋይህን ኪዳን አፈረስህ፥ ዘውዱንም በምድር አረከስህ።
40 ቅጥሩን ሁሉ አፈራረስህ፤ ምሽጉንም ደመሰስህ።
40 ቅጽሮቹን አፈራርሰሃል፤ ምሽጎቹንም ደምስሰሃል።
ቅርንጫፎችዋንም እስከ ባሕር፥ ቡቃያዋንም እስከ ወንዙ ዘረጋች።
ቤት። ጌታ የያዕቆብን ማደሪያዎች ሁሉ ዋጠ፥ አልራራምም፥ በመዓቱ የይሁዳን ሴት ልጅ አምቦች አፈረሰ፥ ወደ ምድርም አወረዳቸው መንግሥቱንና አለቆችዋን አረከሰ።
ሄ። ጌታ እንደ ጠላት ሆነ፥ እስራኤልን ዋጠ፥ አዳራሾችዋን ሁሉ ዋጠ፥ አምቦችዋን አጠፋ፥ በይሁዳም ሴት ልጅ ኀዘንና ልቅሶ አበዛ።
እርሱንና ቤቱን በዙሪያውም ያሉትን ሁሉ አላጠርህለትምን? የእጁን ሥራ ባርከህለታል፥ ንብረቱም በምድር ላይ በዝቶአል።
በምድርም በሚኖሩት ሁሉ ላይ ታላቅ ሁከት ስለ ነበር በዚያም ዘመን ለሚወጣውና ለሚገባው ሰላም አልነበረውም።
ክብሬን ገፈፈኝ፥ ዘውዴንም ከራሴ ላይ ወሰደ።
ቁጣዬንም አፈስስብሃለሁ፥ በመዓቴም እሳት አነድብሃለሁ፥ ማጥፋትንም ለሚያውቁ ለጨካኞች ሰዎች እጅ አሳልፌ እሰጥሃለሁ።