Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 89:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 እርሱ፦ አባቴ አንተ ነህ፥ አምላኬ የመድኃኒቴም መጠጊያ ይላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 እኔም ደግሞ በኵሬ አደርገዋለሁ፤ ከምድር ነገሥታትም በላይ ከፍ ይላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ከምድር ነገሥታትም ሁሉ በላይ እንዲሆን የብኲርናን ማዕርግ እሰጠዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 89:27
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርሱም አካሉ የሆነችው የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፤ እርሱ በሁሉ ነገር ቀዳሚ በመሆን መጀመሪያ ነው፤ ከሙታንም በኩር ነው።


እርሱም ለማይታየው አምላክ ምሳሌ ነው፤ የፍጥረት ሁሉ በኩር ነው፤


በልብሱና በጭኑም ላይ “የነገሥታት ንጉሥና የጌታዎች ጌታ” የሚል ስም ተጽፎአል።


ትእዛዙን እናገራለሁ፥ ጌታ አለኝ፦ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለድሁህ።”


አስቀድሞ ያወቃቸውን የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ወስኖአልና፥ ይህም ከብዙ ወንድሞች መካከል እርሱ በኩር እንዲሆን ነው፤


ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል። አሕዛብም ሁሉ ይገዙለታል።


ከማድጋዎቹ ውኃ ይፈስሳል፥ ዘሩም በብዙ ውኆች ይሆናል፥ ንጉሡም ከአጋግ ይልቅ ከፍ ከፍ ይላል፥ መንግሥቱም ይከበራል።


የእስራኤል ታዳጊ ቅዱሱም፥ ጌታ፥ ሰዎች በሚንቁት ሕዝብም ለሚጠላው፥ ለገዢዎች አገልጋይ እንዲህ ይላል፦ ‘ስለ ታማኙ ስለ ጌታ ስለ መረጠህም ስለ እስራኤል ቅዱስ ነገሥታት አይተው ይነሣሉ፥ መሳፍንትም አይተው ይሰግዳሉ።’


ፈርዖንንም ትለዋለህ፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ እስራኤል የበኩር ልጄ ነው፤


አሕዛብም በብርሃንዋ ይመላለሳሉ፤ የምድርም ነገሥታት ክብራቸውን ወደ እርሷ ያመጣሉ፤


ጥበብንና እውቀትን ሰጥቼሃለሁ፤ ከአንተ በፊትም ከነበሩት ከአንተም በኋላ ከሚነሡት ነገሥታት አንድም እንኳ የሚመስልህ እንዳይኖር አድርጌ ባለጠግነትንና ሀብትን ክብርንም እሰጥሃለሁ።”


“ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፥ ወፈረ፥ ደነደነ፥ ሰባ፥ የፈጠረውንም አምላክ ተወ፥ የመድኃኒቱንም አምላክ ናቀ።


አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል። በደል በሚፈጽምበትም ጊዜ ሰዎች በሚቀጡበት በትር እቀጣዋለሁ፤ የሰው ልጆችም በዐለንጋ እንደሚገረፉ እገርፈዋለሁ።


ጌታ ሕያው ነው! ዐለቴ የተባረከ ይሁን፤ የመዳኔ ዓለት አምላኬ ከፍ ከፍ ይበል።


ሁልጊዜ የምጠጋበት ዓለት ሁነኝ፥ ጠንካራ መሸሸጊያ፥ ዓለቴና መጠጊያዬ አንተ ነህና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች