Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 86:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ታማኝ ነኝና ነፍሴን ጠብቅ፥ አምላኬ ሆይ፥ በአንተ የታመነውን አገልጋይህን አድነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ለአንተ የተለየሁ ሰው ነኝና ነፍሴን ጠብቃት፤ አንተ አምላኬ ሆይ፤ በአንተ የታመነብህን ባሪያህን አድን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እኔ ለአንተ ታማኝ ስለ ሆንኩ ሕይወቴን ጠብቃት፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ በአንተ የምታምነውን እኔን አገልጋይህን አድነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ከያ​ዕ​ቆብ ድን​ኳ​ኖች ይልቅ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጽ​ዮ​ንን ደጆች ይወ​ድ​ዳ​ቸ​ዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 86:2
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እናንት የሰው ልጆች፥ እስከ መቼ ድረስ ክብሬን ታዋርዳላችሁ? ከንቱ ነገርን ለምን ትወድዳላችሁ? ሐሰትንም ለምን ትሻላችሁ?


አምላኬ፥ በአንተ ታመንሁ፥ አልፈር፥ ጠላቶቼ በእኔ አይሣቁብኝ።


ከዚህም በኋላ በዓለም አይደለሁም፤ እነርሱ ግን በዓለም ናቸው፤ እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ። ቅዱስ አባት ሆይ! እነዚህን የሰጠኸኝ እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ በስምህ ጠብቃቸው።


እኔ የአንተ ነኝ፥ ፍርድህን ፈልጌአለሁና አድነኝ።


ለመዘምራን አለቃ፥ በማድነቅ ጊዜ፥ የዳዊት መዝሙር።


በመከራዬ ቀን ደረሱብኝ፥ ጌታ ግን ድጋፍ ሆነኝ።


የዳዊት ቅኔ። አቤቱ፥ በአንተ ታምኛለሁና ጠብቀኝ።


ጠላቴ፦ “አሸነፍሁት እንዳይል”፥ የሚያስጨንቁኝም እኔ ብናወጥ ደስ እንዳይላቸው።


እንግዲህ የፈለገውን ይምረዋል የፈለገውንም እልከኛ ያደርገዋል።


የሚያገለግለኝ ቢኖር ይከተለኝ፤ እኔም ባለሁበት አገልጋዬ ደግሞ በዚያ ይሆናል፤ የሚያገለግለኝም ቢኖር አብ ያከብረዋል።


በጽኑ ፍቅርህ ጠላቶቼን ደምስሳቸው፥ እኔ ባርያህ ነኝና ነፍሴን የሚያስጨንቁአትን ሁሉ አጥፋቸው።


“ከእኔ ጋር በመሥዋዕት ኪዳን ያቆሙትን ቅዱሳኑን ሰብስቡልኝ” ይላል።


ጌታ ፍርድን ይወድዳልና፥ ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና፥ ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል ለንጹሓንም ይበቀልላቸዋል፥ የክፉዎች ዘር ግን ይጠፋል።


የብዙ ሰዎችን ስድብ ሰምቻለሁና፥ በዙሪያው ፍርሃት ነበረ፥ በላዬ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ ነፍሴን ለመንጠቅ ተማከሩ።


እርሱ የታማኞቹን እግር ይጠብቃል ሰው በኃይሉ አይበረታምና፥ ኃጥአን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይጣላሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች