Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 85:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በውኑ ለዘለዓለም ትቈጣናለህን? ቁጣህንስ ለልጅ ልጅ ታስረዝማለህን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ሕዝብህ በአንተ ሐሤት ያደርግ ዘንድ፣ መልሰህ ሕያዋን አታደርገንምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እኛ ሕዝብህ በአንተ እንደሰት ዘንድ፥ እንደገና ሕይወትን አትዘራብንምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን አድ​ምጥ፥ የል​መ​ና​ዬ​ንም ቃል ስማ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 85:6
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ ሆይ፥ ዝናህን ሰምቻለሁ፥ በሥራህም ጌታ ሆይ ፈራሁ፥ በዓመታት መካከል አድሰው፥ በዓመታት መካከል አስታውቀው፥ በቁጣ ጊዜ ምሕረትን አስብ።


እጅህ በቀኝህ ሰው ላይ፥ ለአንተ ባጸናኸው በሰው ልጅ ላይ ትሁን።


ለዘለዓለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፥ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፦ የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።


በማለዳ ጽኑ ፍቅርህን እንጠግባለን፥ በዘመናችን ሁሉ ደስ ይለናል፥ ሐሤትም እናደርጋለን።


ከሁለት ቀን በኋላ ነፍስ ይዘራብናል፤ በሦስተኛውም ቀን ያስነሣናል፥ በፊቱም በሕይወት ያኖረናል።


ብዙ ጭንቀትንና መከራን አሳይተኸኛልና፥ ተመለስህ ሕያውም አደረግኸኝ፥ ከምድር ጥልቅም እንደገና አወጣኸኝ።


በዚያ የሚያስፈራ ሳይኖር እጅጉን ፈሩ፥ እግዚአብሔር የከበቡህን አጥንቶች በትኖአልና፥ እግዚአብሔር ንቆአቸዋልና አሳፈርሃቸው።


በመከራ መካከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ሕያው ታደርገኛለህ፥ በጠላቶቼ ቁጣ ላይ እጆቼን ትዘረጋለህ፥ ቀኝህም ታድነኛለች።


እርሱም፦ የሐሤት ድምፅና የደስታ ድምፅ፥ የሙሽራው ድምፅና የሙሽራይቱ ድምፅ፥ ወደ ጌታም ቤት፦ ‘ጌታ ቸር ነውና፥ ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና የሠራዊት ጌታን አመስግኑ!’ እያሉ የምስጋናን መሥዋዕት የሚያመጡ ሰዎች ድምፅ ነው። የምድሪቱን ምርኮ ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ እመልሳለሁና፥ ይላል ጌታ።


እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይበለው፥ የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤትን ያድርጉ።


የአሳፍ ትምህርት። አቤቱ፥ ስለምን ለሁልጊዜ ጣልኸኝ? በማሰማርያህ በጎች ላይስ ቁጣህ ስለምን ጨሰ?


ጌታ ለዘለዓለም ይጥላልን? እንግዲህስ ቸርነቱን አይጨምርምን?


‘ለዘለዓለምስ ይቈጣልን? እስከ ፍጻሜስ ድረስ ይጠብቀዋልን?’ እነሆ፥ እንዲህ ብለሽ ተናገርሽ፥ እንደ ተቻለሽም መጠን ክፉን ነገሮች አደረግሽ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች