Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 85:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 መዓትህንም ሁሉ አስወገድህ፥ ከቁጣህ መቅሠፍት ተመለስህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 መድኀኒታችን የሆንህ አምላክ ሆይ፤ መልሰን፤ በእኛ ላይ የተቃጣውን ቍጣህን መልሰው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 አዳኛችን እግዚአብሔር ሆይ! ከተሰደድንበት መልሰን፤ በእኛም ላይ ያለህን ቅርታ አርቅልን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የባ​ሪ​ያ​ህን ነፍስ ደስ አሰ​ኛት፥ ነፍ​ሴን ወደ አንተ አነ​ሣ​ለ​ሁና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 85:4
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አምላኬ፥ በአንተ ታመንሁ፥ አልፈር፥ ጠላቶቼ በእኔ አይሣቁብኝ።


ሳይቀባ፥ የዳዊት መዝሙር። ጌታ ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፥ የሚያስፈራኝ ማን ነው? ጌታ የሕይወቴ ከለላዋ ነው፥ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?


እርሱ ግን ርኅሩኅ ነው፥ በደላቸውንም ይቅር አላቸው፥ አላጠፋቸውምም፥ ከቁጣውም መመለስን አበዛ፥ መዓቱንም ሁሉ አላቃጠለም።


ከአንተም አንራቅ፥ አድነን ስምህንም እንጠራለን።


በኤፍሬምና በብንያም በምናሴም ኃይልህን አንሣ እኛንም ለማዳን ና።


ለጎረቤቶቻችን መከራከርያ አደረግኸን፥ ጠላቶቻችንም ይሣለቁብናል።


በአንተ ላይ ያመጣሁትን ቅጣት በጥቂት ጊዜ ውስጥ አቆማለሁ፤ በእነርሱም ላይ መዓቴን አመጣለሁ።”


በዚያን ቀን እንዲህ ትላለህ፤ “ጌታ ሆይ፤ ቀድሞ ተቈጥተኸኝ ነበር፤ አሁን ግን ከቁጣህ ተመለስህ፤ ደግሞም አጽናንተኸኛልና እወድስሃለሁ።


በእውነት ኤፍሬም ሲያለቅስ ሰማሁ፦ ‘ቀጣኸኝ እኔም እንዳልተገራ ወይፈን ተቀጣሁ፤ አንተ ጌታ አምላኬ ነህና መልሰኝ እኔም እመለሳለሁ።


አቤቱ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፥ ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ።


እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና፥ በመካከልህም ቅዱሱ ነኝና የቁጣዬን መቅሠፍት አላደርግም፥ ኤፍሬምንም ዳግመኛ አላጠፋም፤ በመዓትም አልመጣም።


እኔ ግን ወደ ጌታ እመለከታለሁ፥ የመድኃኒቴን አምላክ እጠብቃለሁ፤ አምላኬ ይሰማኛል።


መጥቼ ምድርን በእርግማን እንዳልመታ፥ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶቻቸው ይመልሳል።


እናንተስ ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ ለምናውቀው እንሰግዳለን፥ መዳን ከአይሁድ ነውና።


በእርሱም ላይ እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩ፤ ጌታም ከጽኑ ቁጣው ተመለሰ። ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የአኮር ሸለቆ ተብሎ ተጠራ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች