Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 83:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የኤዶማውያን ድንኳኖች እስማኤላውያንም፥ ሞዓብም አጋራውያንም፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ጌባል፣ አሞንና አማሌቅ፣ ፍልስጥኤምም ከጢሮስ ሕዝብ ጋራ ሆነው ዶለቱ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የጌባል፥ የዐሞን፥ የዐማሌቅ፥ የፍልስጥኤምና የጢሮስ ሰዎች ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ከኀ​ይል ወደ ኀይ​ልም ይሄ​ዳል፥ የአ​ማ​ል​ክት አም​ላክ በጽ​ዮን ይታ​ያል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 83:7
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሳኦልም ዘመን ከአጋራውያን ጋር ተዋጉ፥ እነርሱም በእጃቸው ተመትተው ወደቁ፤ በገለዓድ ምሥራቅ በኩል ባለው አገር ሁሉ በድንኳኖቻቸው ተቀመጡ።


በባሕር መግቢያ ለምትኖረውና፥ በብዙ ደሴቶች ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ጋር ለምትነግደው ጢሮስ እንዲህ በላት፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ፥ አንቺ፦ “በውበት ፍጹም ነኝ” ብለሻል።


በአንቺ ውስጥ የነበሩ የጌባል ሽማግሌዎችና ጥበበኞችዋ ስብራትሽን ይጠግኑ ነበር፤ የባሕር መርከቦች ሁሉና መርከበኞቻቸው ከአንቺ ጋር ለመለዋወጥ በአንቺ ውስጥ ነበሩ።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ “በምርኮ የሄዱትን ሕዝብ ሁሉ ለኤዶምያስ አሳልፈው ሰጥተዋልና፥ የወንድማማቾችንም ቃል ኪዳን አላስታወሱምና ስለ ሦስት የጢሮስ ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።


የጌባላውያንም ምድር፥ በፀሐይም መውጫ በኩል ከአርሞንዔም ተራራ በታች ካለችው በኣልጋድ ጀምሮ እስከ ሐማት መግቢያ ድረስ ያለችው ሊባኖስ ሁሉ፥


የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፤ ‘እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ፥ አማሌቃውያን በመንገድ ላይ ስለ ተቃወሙት እቀጣቸዋለሁ።


የሳሙኤልም ቃል ወደ እስራኤል ሁሉ ደረሰ። በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያንን ሊወጉ ወጡ፤ እነርሱ በአቤንኤዘር ሲሰፍሩ፥ ፍልስጥኤማውያን ደግሞ በአፌቅ ሰፈሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች