Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 79:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ፥ እርዳን፥ ስለ ስምህ ክብር፥ አቤቱ፥ ታደገን፥ ስለ ስምህም ኃጢአታችንን አስተሰርይልን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 አዳኛችን የሆንህ አምላክ ሆይ፤ ስለ ስምህ ክብር ብለህ ርዳን፤ ስለ ስምህ ስትል፣ ታደገን፤ ኀጢአታችንንም ይቅር በል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 አዳኛችን አምላክ ሆይ! እርዳን፤ ስለ ራስህ ክብር ስትል ተቤዠን፤ ኃጢአታችንንም ይቅር በልልን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በፊ​ቷም መን​ገ​ድን ጠረ​ግህ፥ ሥሮ​ች​ዋ​ንም ተከ​ልህ፥ ምድ​ር​ንም ሞላች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 79:9
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አሳም እንዲህ ብሎ ወደ አምላኩ ወደ ጌታ ጮኸ፦ “አቤቱ፥ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አይሳንህምና፤ አቤቱ አምላካችን ሆይ! በአንተ ታምነናልና፥ በስምህም በዚህ ታላቅ ወገን ላይ መጥተናልና እርዳን፤ አቤቱ፥ አምላካችን አንተ ነህ፤ ሰውም አያሸንፍህ።”


ለእኛ አይደለም፥ አቤቱ፥ ለእኛ አይደለም፥ ነገር ግን ለስምህ ስለ ጽኑ ፍቅርህና ስለ እውነትህም ክብርን ስጥ።


አቤቱ፥ በደሌ ብዙ ነውና ስለ ስምህ ይቅር በለኝ።


ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፥ ፈጥነህም አድነኝ፥ ታድነኝ ዘንድ መታመኛ አምላክና የመጠጊያ ቤት ሁነኝ።


ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ሥጋ ሁሉ ይመጣል።


መተላለፍህን፦ ስለ እኔ ስል የምደመስስ እኔ ነኝ፤ ኃጢአትህንም አላስብም።


ስለ ስሜ ቁጣዬን አዘገያለሁ፥ እንዳለጠፋህም ስለ ምስጋናዬ እታገሣለሁ።


ስለ ስምህ ብለህ አትናቀን፥ የክብርህንም ዙፋን አታዋርድ፤ ከእኛ ጋርም ያደረግኸውን ቃል ኪዳንህን አስታውስ እንጂ አታፍርስ።


“ኃጢአታችን ብዙ ነውና፥ በአንተም ላይ ኃጢአትን ሠርተናል፤ ምንም እንኳ ኃጢአታችን ቢመሰክርብንም ስለ ስምህ ብለህ አቤቱ! አድርግ።


ነገር ግን በፊታቸው ባወጣኋቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።


የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እንደ ክፉ መንገዳችሁና እንደ ርኩስ ሥራችሁ ሳይሆን ስለ ስሜ ስል በሠራሁላችሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ነገር ግን በመካከላቸው ባሉ ከግብጽም ምድር አወጣቸው ዘንድ በፊታቸው በተገለጥሁላቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።


“ባትሰሙ፥ ለስሜም ክብር ለመስጠት በልባችሁ ባታኖሩት፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፥ “እርግማን እልክባችኋለሁ፥ በረከታችሁንም እረግማለሁ፤ አሁንም ረግሜዋለሁ ምክንያቱም በልባችሁ አላደረጋችሁትምና።”


በውድ ልጁም በነጻ የሰጠን የከበረ ጸጋው እንዲመሰገን ይህን አደረገ።


ከነዓናውያንም በምድሪቱ የሚኖሩ ሁሉ ሰምተው ይከብቡናል፥ ስማችንንም ከምድር ያጠፋሉ፤ ለታላቁ ስምህም የምታደርገው ምንድነው?”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች