39 ወጥቶ የማይመለስ ነፋስ፥ ሥጋም እንደ ሆኑ አሰበ።
39 ወጥቶ የማይመለስ ነፋስ፣ ሥጋ ለባሾች መሆናቸውን ዐሰበ።
39 ካለፈ በኋላ እንደማይመለስ ነፋስ፥ ሟች ፍጥረቶች መሆናቸውን አስታወሰ።
ነገ የሚሆነውን አታውቁም። ሕይወታችሁ ምንድነው? ለጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፋሎት አይደላችሁምን?
“ሕይወቴ እስትንፋስ እንደሆነ አስታውስ፥ ዓይኔ መልካም ነገርን ከእንግዲህ ወዲህ አያይም።
ጌታም፦ “መንፈሴ በሰው ላይ ለዘለዓለም አይኖርም፥ እርሱ ሥጋ ነውና፥ እድሜውም መቶ ሃያ ዓመት ይሆናል” አለ።
ሕይወቴን ናቅኋት፥ ለዘለዓለም ልኖር አልወድድም፥ ቀኖቼ እስትንፋስ ናቸውና ተወኝ።
ከጭቃ እንደሠራኸኝ አስታውስ፥ ወደ ትቢያም ትመልሰኛለህን?
ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።