33 ቀኖቻቸውም በከንቱ አለቁ፥ ዓመቶቻቸውም በሽብር።
33 ስለዚህ ዘመናቸውን በከንቱ፣ ዕድሜያቸውንም በድንጋጤ ጨረሰ።
33 ስለዚህ ዕድሜአቸውን እንደ እስትንፋስ አሳጠረ፤ ሕይወታቸውም በሽብር እንዲያልቅ አደረገ።
እኔ ጌታ፦ በእኔ ላይ በተሰበሰበ በዚህ ክፉ ማኅበር ሁሉ ላይ በእውነት እንዲህ አደርጋለሁ ብዬ ተናገርሁ፤ በዚህ ምድረ በዳ ያልቃሉ፥ በዚያም ይሞታሉ።”
በድኖቻችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃሉ፤ ከአጠቃላይም ቁጥራችሁ፥ በእኔ ላይ ያጉረመረሙ ዕድሜአቸው ሀያ ዓመት የሆናቸውና ከዚያም በላይ ሆነው የተቈጠሩት ሁሉ፥
ሰባኪው፦ ከንቱ፥ ከንቱ፥ ሁሉ ከንቱ ነው ይላል።
ሰባኪው፦ ከንቱ፥ ከንቱ፥ የከንቱ ከንቱ፥ ሁሉ ከንቱ ነው ይላል።
“ከሴት የተወለደ ሰው የሕይወቱ ዘመን ጥቂት ቀን ነው፥ በመከራም የተሞላ ነው።
ልጆቻችሁም በምድረ በዳ አርባ ዓመት እረኛች ይሆናሉ፥ በድኖቻችሁም በምድረ በዳ እስኪጠፉ ድረስ ዝሙታችሁን ይሸከማሉ።