16 ውኃን ከዓለት አወጣ፥ ውኃንም እንደ ወንዞች አፈሰሰ።
16 ምንጭ ከቋጥኝ አፈለቀ፤ ውሃን እንደ ወንዝ አወረደ።
16 ምንጭን ከአለት አፈለቀ፤ ውሃውም እንደ ወንዝ እንዲፈስስ አደረገ።
ዓለቱን ሰነጠቀ፥ ውኃውም ፈለቀ፥ ወንዞች በበረሃ ፈሰሱ፥
ምድረ በዳን ወደ ውኃ ማጠራቀምያ፥ ደረቁንም ምድር ወደ ውኃ ምንጭነት ቀየረ።
በያዕቆብ አምላክ ፊት፥ በጌታ ፊት ምድር ተናወጠች፥
ዐለቱን ወደ ውኃ መቆሚያ፥ ድንጋዩንም ወደ ውኃ ምንጭ ይለውጣል።
ቀስትህን ገለጥህ በቃልህ እንደ ማልህ መቅሠፍትህን አወጣህ፤ ቀስትህንም ገተርህ፤ ምድርን ሰንጥቀህ ፈሳሾችን አወጣህ።
“በትሩን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮን ማኅበሩን ሰብስቡ፥ እነርሱም ዓይናቸው እያየ ድንጋዩ ውኃን እንዲሰጥ ተናገሩት፤ ለእነርሱም ከድንጋዩ ውኃ ታወጣላቸዋለህ፤ እንዲሁም ለማኅበሩና ለከብቶቻቸው የሚጠጣ ወኃ ትሰጣቸዋለህ።”
መርዘኛ እባብና ጊንጥ ጥማትም ባለባት፥ ውኃም በሌለባት በታላቂቱና በምታስፈራው ምድረ በዳ የመራህን፥ ከዓለት ድንጋይም ውኃን ያፈለቀልህን፥
የሠራችሁትንም ጥጃ ምስል፥ ኃጢአት ያደረጋችሁበትንም ወሰድሁ፥ በእሳትም አቃጠልሁት፥ አደቀቅሁትም፥ እንደ ትቢያም እስኪሆን ድረስ ፈጨሁት፥ ትቢያውንም ከተራራ በሚወርድ ወንዝ ጣልሁት።