Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 77:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በመከራዬ ቀን ጌታን ፈለግሁት፥ እጆቼ በሌሊት በፊቱ ናቸው፥ አላረፍሁምም፥ ነፍሴም መጽናናትን አልቻለችም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 አምላክ ሆይ፤ አንተን ባሰብሁ ቍጥር ቃተትሁ፤ ባወጣሁ ባወረድሁም መጠን መንፈሴ ዛለች። ሴላ

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ስለ እግዚአብሔር በማስብበት ጊዜ እተክዛለሁ፤ በጥሞና ሳሰላስል መንፈሴ ይዝላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የሰ​ማ​ነ​ው​ንና ያየ​ነ​ውን፥ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም የነ​ገ​ሩ​ንን፥ ለሚ​መጣ ትው​ልድ ከል​ጆ​ቻ​ቸው አል​ሰ​ወ​ሩም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 77:3
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አምላክ ሆይ፥ ጩኸቴን ስማ፥ ጸሎቴንም አድምጥ።


የእግዚአብሔር መዓት አስደንግጦኛልና፥ በክብሩም ፊት ምንም ለማድረግ አልቻልሁም።”


ሕያው ሰው የሚያጉረመርም፥ ሰው ስለ ኃጢአቱ ቅጣት የሚያጉረመርም ስለ ምንድነው?


ለማስፈራራት አትሁንብኝ፤ በመከራ ቀን አንተ መጠጊያዬ ነህ።


ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ።


ጠላቶቼ ሁልጊዜ፦ አምላክህ ወዴት ነው? ባሉኝ ጊዜ አጥንቶቼን እየቀለጣጠሙ ሰደቡኝ።


ይህን ሳስብ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ፈሰሰች፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ምስጋና መኖሪያ ስፍራ እገባለሁና፥ በዓል የሚያከብሩ ሰዎች የደስታና ምስጋና ቃል አሰሙ።


“ስለዚህም ከመናገር አፌን አልከለክልም፥ በመንፈሴ ጭንቀትን እናገራለሁ፥ በነፍሴ ምሬት በኀዘን አንጐራጉራለሁ።


ሁሉን የሚችል የአምላክ ፍላጻ በሥጋዬ ውስጥ ነው፥ መርዙንም ነፍሴ ትጠጣለች፥ የእግዚአብሔር ሽብሮች በኔ ላይ ተሰልፈዋል።


ነፍሴን ከሰላም አራቅህ፥ በጎ ነገርን ረሳሁ።


ወንዶች ልጆቹና ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት ተነሡ፥ መጽናናትን እንቢ አለ፥ እንዲህም አለ፦ “ወደ ልጄ ወደ ሙታን ስፍራ እያዘንሁ እወርዳለሁ።” አባቱም እንደዚህ ስለ እርሱ አለቀሰ።


በውኑ የእግዚአብሔር ማጽናናት፥ በየውሃትም የተነገረህ ቃል ጥቂት ነውን?


በመከራ ቀን ጥራኝ፥ አድንህማለሁ አንተም ታከብረኛለህ።


ሌሊት በመኝታዬ ላይ ነፍሴ የወደደችውን ፈለግሁት፥ ፈለግሁት አላገኘሁትም።


አቤቱ ጌታ፥ በመከራ ጊዜ ፈለጉህ፥ በገሠጽሐቸውም ጊዜ ልመናቸውን ወደ አንተ አፈሰሱ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች