Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 77:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ይህ ድካሜ ነው አልሁ፥ የልዑል ቀኝ መለወጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የእግዚአብሔርን ሥራ አስታውሳለሁ፤ የጥንት ታምራትህን በርግጥ አስታውሳለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እግዚአብሔር ሆይ! ያከናወንካቸውን ታላላቅ ሥራዎች አስታውሳለሁ፤ ባለፉት ዘመናት ያደረግኻቸው ተአምራት ትዝ ይሉኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ረድ​ኤ​ቱ​ንና ያሳ​ያ​ቸ​ውን ተአ​ም​ራ​ቱን ረሱ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 77:11
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የቀድሞውን ዘመን አሰብሁ፥ ሥራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ፥ የእጅህንም ሥራ አስተዋልሁ።


አገልጋዮቹ የአብርሃም ዘር፥ ለእርሱም የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ የሠራውን ድንቅ ሥር አስቡ፥ ተአምራቱን የተናገረውንም ፍርድ።


ተአምራቱንም የተናገረውንም ፍርድ፥ የሠራትን ድንቅ አስቡ፤ እናንተ


በግብዣቸው ላይ በገናና መሰንቆ፤ ከበሮና ዋሽንት እንዲሁም የወይን ጠጅ አለ፤ ነገር ግን ለጌታ ሥራ ቦታ አልሰጡም፤ ለእጆቹም ሥራ ክብር አላሳዩም።


ወደ ጌታ ሥራ ወደ እጆቹም አደራረግ አላሰቡምና ያፈርሳቸዋል እንጂ አይሠራቸውም።


ለተአምራቱ መታሰቢያን አደረገ፥ ጌታ መሓሪና ርኅሩኅ ነው።


መልካም ሥራውንና ያሳያቸውን ተኣምራቱን ረሱ፥


እግዚአብሔርስ ማዘኑን ረሳን? በቁጣውስ ርኅራኄውን ዘጋውን?


ይስሐቅም በመሸ ጊዜ በልቡ እያሰላሰለ ወደ ሜዳ ወጥቶ ነበር፥ ዐይኖቹንም አቀና፥ እነሆም ግመሎች ሲመጡ አየ።


ከአማልክት መካከል ጌታ ሆይ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በቅድስና ባለግርማ፥ በምስጋና የተፈራህ፥ ድንቅንም የምታደርግ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች